አዲስ ጊዜ

230 Posts
የወሎ ተርሸሪ ሆስፒታል ግንባታ የት ደረሰ ?

የወሎ ተርሸሪ ሆስፒታል ግንባታ የት ደረሰ ?

የፌደራል ዋና ኦዲተር የ2015 በጀት ዓመት የፌደራል መንግሥት ተቋማትን የበጀት ኦዲት ዋና ዋና ግኝቶችን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል። ዋና ኦዲተር በሪፖርቱ ላይ እንዳለው ከህዝብ በቀረበለት ጥያቄ መሰረት ኦዲት ካደረጋቸው ስራዎች መካከል የወሎ ተርሸሪ የህክምና እና የማስተማሪያ ሆስፒታል ግንባታ ዋነኛው ነው፡፡ በተሰራው የኦዲት ሪፖረት መሰረትም ለሆስፒታሉ ግንባታ በሚል የገቢ ማሰባሰቢያ በሀገር ውስጥ እና ውጭ ሀገራት ሲደረግ እንደነበር ተገልጿል፡፡ ለዚህም ሲባል በውጭ ሀገራት በሚገኙ የኢትዮጵያ ኢምባሲዎች እና ቆንስላ ጽህፈት ቤቶች፣ ክልሎች እና ሌሎች አካባቢዎች ይሸጣል ተብሎ 9 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ኩፖን ተሰራጭቶ እንደነበር በሪፖርቱ ላይ ተገልጿል፡፡ ይሁንና ይህ 9 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር የሚያወጣው የገቢ መሰብሰቢያ…
ተጨማሪ ያንብቡ
ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው፣ በላይ ማናዬ እና ቴዎድሮስ ዘርፉ ከእስር ተፈቱ

ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው፣ በላይ ማናዬ እና ቴዎድሮስ ዘርፉ ከእስር ተፈቱ

ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አቤቱታ ያቀረቡት ሶስት ጋዜጠኞች ከእስር ተፈቱ። ዛሬ እና ከትላንት በስቲያ ቅዳሜ ከእስር የተለቀቁት ጋዜጠኞች በቃሉ አላምረው፣ በላይ ማናዬ፣ ቴዎድሮስ ዘርፉ ናቸው።  በትናንትናው ዕለት ከእስር የተፈቱት ሶስቱ ጋዜጠኞች የፌደራል ፖሊስ “ሕገ መንግስታዊ መብታቸውን በመጣስ በእስር እንዲቆዩ” ማድረጉን በመጥቀስ ለፍርድ ቤት “አካልን ነጻ የማውጣት” አቤቱታ ያቀረቡት ባለፈው ሳምንት ነበር። ከአቤቱታ አቅራቢዎች አንዱ የሆነው የ“ኢትዮ ኒውስ”  የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃን መስራች እና አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ በላይ ሰኞ ሰኔ 10፤ 2016 የተፈታ ሲሆን አስር ወራትን በአዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ በእስር ያሳለፈው ሌላኛው ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ፤ ባለፈው አርብ ሰኔ 7፤ 2016 ወደ አዲስ አበባ እንዲመጣ ከተደረገ በኋላ…
ተጨማሪ ያንብቡ
“ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ” የተሰኘው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት፤ በኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እና በጋዜጠኞች ላይ የሚፈጸመው  እስር አሳስቦኛል አለ

“ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ” የተሰኘው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት፤ በኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እና በጋዜጠኞች ላይ የሚፈጸመው  እስር አሳስቦኛል አለ

 “ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ” የተሰኘው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት በጋዜጠኞች፣ በኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ በማህበራዊ ሚዲያ ተጽእኖ ፈጣሪዎች እንዲሁም በፖለቲከኞች ላይ እየተፈጸመ ያለው “የዘፈቀደ እስር” እንዳሳሰበው ትናንት አርብ ግንቦት 30፤ 2016 ባወጣው መግለጫ አሳውቋል ። እርምጃው “በአሳሳቢ ሁኔታ እየጠበበ የመጣውን የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት እና ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት የማፈን አዝማሚያን የሚያመለክት ነው” ብሏል ድርጅቱ። ሀገር በቀሉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት በኢትዮጵያ በርካቶች ስለሚጋፈጧቸው እውነታዎች የዘገቡ እና አመለካከታቸውን ያንጸባረቁ ግለሰቦች መታሰራቸውን አስታውቋል። የግለሰቦቹ መታሰር፤ መሰረታዊ የሆኑትን የሰብዓዊ መብቶች “በግልጽ የሚጥስ” መሆኑን በመጥቀስም ድርጅቱ ተችቷል። ኪነ ጥበብ በሰብአዊ መብት ዙሪያ ያለን ግንዛቤን ለማሳደግ “ወሳኝ ሚና” እንደሚጫወት የጠቀሰው የድርጅቱ መግለጫ፤ በኪነ…
ተጨማሪ ያንብቡ
በሀገራዊ ምክክሩ ላይ አዲስ አበባን የወከሉ ወኪሎች የምክክር አጀንዳዎችን ለኮሚሽኑ አስረከቡ

በሀገራዊ ምክክሩ ላይ አዲስ አበባን የወከሉ ወኪሎች የምክክር አጀንዳዎችን ለኮሚሽኑ አስረከቡ

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በመወከል በሀገራዊ ምክክር የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ሲሳተፉ የቆዩ ተወካዮች ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 27፣ 2017 በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደ የርክክብ ስነ ስርዓት፤ ፤ በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ላይ “ሊመከርባቸው ይገባሉ” ብለው የመረጧቸውን ጉዳዮች ለሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ምክር ቤት አስረከቡ። ተወካዮቹ አጀንዳዎቻቸውን በስምንት ርዕሰ ጉዳዮች በመከፋፈል  ያቀረቡ ሲሆን ከእነዚህ ርዕሰ ጉዳዮች መካከል የአዲስ አበባ ባለቤትነት እና አወቃቀር፣ ቋንቋ፣  ታሪክ እና ትርክት፣ የሃገረ መንግስት ግንባታ እና የሃገር አንድነትን፣ የአንድነት እና ብዝሃነትን የሰንደቅ አላማ እና የህገ መንግስት ጉዳዮችን የተመለከቱ ይገኙበታል ተብሏል። አሁን በስራ ላይ ካለውን የኢፌዲሪ ህገ መንግስት…
ተጨማሪ ያንብቡ
መንግስት በፈፀማቸው  የድሮን ጥቃቶች 10 ሰዎች መገደላቸውን ኢሰመኮ ገለጸ

መንግስት በፈፀማቸው  የድሮን ጥቃቶች 10 ሰዎች መገደላቸውን ኢሰመኮ ገለጸ

በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ በአፋር፣ በሶማሊ፣ በሲዳማ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ እና በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎችና በአዲስ አበባ ከተማ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ። ኮሚሽኑ ባወጣው የሰብዓዊ መብት ሪፖርት መንግስት ታህሳስ እና ግንቦት ላይ በፈጸማቸው ሁለት የድሮን ጥቃቶች 10 ሰዎች ሲገደሉ ከ10 በላይ ቆስለዋል ብሏል ፡፡ ከሕግ ውጭ ግድያ፣ የሲቪል ሰዎች ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመትና ዘረፋ፣ የዘፈቀደ፣ የጅምላና የተራዘመ እስራትና የተፋጠነ ፍትሕ እጦት፣ አስገድዶ መሰወር፣ እገታ፣ እና የሀገር ውስጥ መፈናቀል እጅግ አሳሳቢ ሆነው የቀጠሉ የመብት ጥሰቶች መሆናቸው ተገልጿል። ኮሚሽኑ በጸጥታ ችግር እና ከመንግስት ተገቢውን ትብብር ባለማግኘት እንዲሁም በሌሎች ምክንያቶች የዘገዩ ምርመራዎች በሂደት…
ተጨማሪ ያንብቡ
ኢትዮጵያ በቀጣይ አራት ወራት ከመደበኛው በላይ ዝናብ እንደምታስተናግድ ኢጋድ ተነበየ።

ኢትዮጵያ በቀጣይ አራት ወራት ከመደበኛው በላይ ዝናብ እንደምታስተናግድ ኢጋድ ተነበየ።

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የአየር ንብረት ትንበያ እና ትግበራ ማዕከል ICPAC በቀጣይ አራት ወራት ማለትም ከሰኔ 2016 እስከ መስከረም 2017 ዓ.ም  ኢትዮጵያን ጨምሮ በምስራቅ አፍሪካ የሚኖረውን የዝናብ እና መጠነ ሙቀት ሁኔታ ትንበያ በደቡብ ሱዳን ጁባ ከተማ ይፋ አድርጓል። ለኢትዮጵያ ክረምት በምንለው እና በሰሜኑ የምስራቅ አፍሪካ ክፍል በክረምት ዝናብ ተጠቃሚ ሀገራት ማለትም ኢትዮጵያ፣ጁቡቲ፣ኤርትሪያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ዮጋንዳና ምዕራብ ኬንያን ጨምሮ በቀጣይ አራት ወራት ከመደበኛው ዝናብ በላይ እንደሚያገኙ የማዕከሉ ባለሞያ የሆኑት ዶክተር ሁሴን ሰዒድ ተናግረዋል። ሁሴን አክለው በተለይ ለምዕራብ፣ደቡብ ምዕራብ፣ሰሜን፣ሰሜን ምስራቅ፣መካከለኛ የኢትዮጲያ ክፍል መጪው የክረምት በጣም ወሳኝ ወቅት ስለሆነ  ከፍተኛ ኤና ከመደበኛ በላይ የሆነ ዝናብ ያስተናግዳሉ። በመሆኑም…
ተጨማሪ ያንብቡ
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ በመንግስት ጫና እየተደረገበት እንደሆነ ገለጸ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ በመንግስት ጫና እየተደረገበት እንደሆነ ገለጸ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) መንግስት ከፍተኛ ጥቃትና ጫና እየፈጸመበት እንደሆነ ባወጣው መግለጫ ገልጿል፡፡ ኢሰመጎ በመግለጫው በመንግስት እየደረሰበት ያለው ጥቃት እና ጫና አስጊ ደረጃ ላይ መድረሱን  አሳውቋል። ጉባኤው በተለያዩ ጊዜ ተፈጽመውብኛል ያላቸው ጥቃቶች እና ከፍተኛ ጫናዎች በመግለጫው ላይ የዘረዘረ ሲሆን በተቋሙ አመራር ላይ በመንግስት የደህንነት ሰዎች የሚፈጸም ክትትል ፣ ዛቻ እና ማስፈራሪያ እየጨመረ መምጣታቸውን አስታውቋል፡፡ እንዲሁም የሰብዓዊ መብት ክትትል ስራችሁን ካላቆማችሁ ፤ መንግሥትን በሰብዓዊ መብት ጥሰት መወንጀል ካላቆማችሁ  ‘ ዋጋ ትከፍላላችሁ ‘ የሚል ዛቻ እየደረሰበት መሆኑን ገልጿል፡፡ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የምርመራ ስራ በሚሰሩ ሰራተኞች ላይ የመንግስት ጸጥታ አካላት አካላዊ ጥቃት ማድረስ፣ መሳደብ፣ ማንገላታት፣ ስራቸውን እንዲያቆሙ ማስፈራራት…
ተጨማሪ ያንብቡ
የኪነጥበብ ስራዎችን ማገድ ሃሳብን በነፃነት መግለጽ መብትን ማገድ ነው-የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል  

የኪነጥበብ ስራዎችን ማገድ ሃሳብን በነፃነት መግለጽ መብትን ማገድ ነው-የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል  

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል  ዋና ዳይሬክተር አቶ ያሬድ ሀይለመስቀል   የኪነ ጥበብ ስራዎች ሀሳብን በነጻነት የመግለጫ መንገድ በመሆናቸው  ከጥቃት ሊጠበቁ እና ባለሙያዎችም ለእስር ሊዳረጉ አይገባም ብለዋል፡፡ መንግስት ለኪነ ጥበብ ሙያ እና ባለሙያዎች ልዩ ጥበቃ ሊያደርግ ይገባል ያሉት አቶ ያሬድ ኪነ-ጥበብ ለሰብአዊ መብቶች ግንዛቤ መዳበር፣ መጎልበት እንዲሁም  መስፋፋት እና መከበር ያለው ጉልህ ሚና እጅግ የላቀ ነው ብለዋል፡፡ በተለይም የኪነ-ጥበብ መድረኮች እና ባለሞያዎች በሙዚቃ፣ በቲያትር፣ በግጥም፣ በስዕል እና በቅርፃቅርፅ መልክ የሚያንጸባርቋቸው ሃሳቦች የዜጎች ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት መገለጫዎች እንደሆኑ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል። እነዚህ የኪነ-ጥበብ ዘርፎች ለአንድ ማህበረሰብ የደስታም ሆነ የብሶት ሃሳቦቹን የሚገልጽባቸው መንገዶች የመሆናቸውን ያህል በአገር አስተዳደር ኃላፊነት ላይ…
ተጨማሪ ያንብቡ
ሌንጮ ባቲ ስለሺ በቀለን ይተካሉ?

ሌንጮ ባቲ ስለሺ በቀለን ይተካሉ?

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው እያገለገሉ የሚገኙት የቀድሞው የውኃ ሀብት ሚኒስትር ስለሺ በቀለ   ከአምባሳደርነት ሹመታቸው እንዲሁም ከማንኛውም የመንግስት ሃላፊነት  በመልቀቅ በግል  በሙያቸው ለማገልገል ማቀዳቸውን እና ጥያቄ ማቅረባቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ መዘገቡ ይታወሳል፡፡ይህንን ተከትሎ አምበሳደር ስለሺ  ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱን ምንጮቻችን ነግረውናል። አምባሳደር ስለሺ በቀለ በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የሥልጣን ዘመን ወቅት የፓርቲ አባል ሳይሆኑ የመንግሥት መዋቅርን መቀላቀላቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ከዚያ አስቀድመው በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በውኃ ምኅንድስና ሙያቸው በግል ተቀጥረው ሲያገለግሉ ነበር። የቀድሞው የአርባምንጭ ዩንቨርሲቲ መምህር ስለሺ በቀለ በአምባሳደርነት ከመሾማቸው በፊት የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ሆነው ከአምስት ዓመት በላይ አገልግለዋል፡፡ አምባሳደር ሽለሺ በታለቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ…
ተጨማሪ ያንብቡ
ጋዜጠኛ ሳሙኤል አሰፋ ከአገር ለመሰደድ መገደዱን ተናገረ

ጋዜጠኛ ሳሙኤል አሰፋ ከአገር ለመሰደድ መገደዱን ተናገረ

ጋዜጠኛ ሳሙኤል አሰፋ በዋዜማ ሬዲዮ፣ ኢኤምኤስ እና ሌሎችም ሚዲያዎች በጋዜጠኝነት ሲሰራ ቆይቷል፡፡ ከወራት በፊት በአዲስ አበባ ዙሪያ ሸገር ከተማ “ሕገ ወጥ ግንባታ” ናቸው ተብለው በፈረሱ ወደ 100 ሺህ የሚቆጠሩ መኖሪያ ቤቶችና በተፈናቀሉ ዜጎች ጉዳይ ለዘገባ ወደ ስፍራው ባመራበት ወቅት በፖሊስ ተይዞ ለእስር ተዳርጎም ነበር፡፡ በዚህ ወቅት በፖሊስ ድብደባ፣ እስርና ማዋከብ ደርሶበት እንደነበር የተናገረው ጋዜጠኛ ሳሙኤል አሰፋ በዋስ ከእስር ቤት ወጥቶ እንዲከራከር በፍርድ ቤት ተወስኖለት ቢወጣም ዛቻና ማስፈራሪ ሲደርስበት እንደነበረ ነግሮኛል ሲል ኢትዮ ነጋሪ አስነብቧል፡፡ በቅርቡም ለዋዜማ ሬድዮ እና ኢንተር ኒውስ ዘገባ ለመስራት ወደ አማራ ክልል ደሴና ሐይቅ ከተሞች በተጓዘበት ወቅት በክልሉ ኮማንድ ፖስት ታስሮ እንደነበረም አክሏል።…
ተጨማሪ ያንብቡ