ደጃዝማች ባልቻ አባነፍሶ እና የቅዱስ ጳውሎስ ሪፈራል ሆስፒታል ላይ ፍርድ ቤት የቅጣት ውሳኔ አስተላለፈ
በ-እታገኘሁ መኮነን በተደጋገሚ የህክምና ስህተት አራት ጊዜ ቀዶ ህክምና ለማድረግ የተገደዱት እና ሁለት ጊዜ ባዕድ ነገር የሰውነት ክፍላቸው ውስጥ የተረሳባቸው ግለሰብ የሁለት ሚሊዮን ብር የካሳ ክፍያ አገኙ፡፡ ግለሰቡ አቶ አስማረ አለሙ ይባላሉ፡፡ የኢሊባቦር በደሌ ነዋሪ ናቸው፡፡ 2006 ላይ ለህክምና ወደ አዲስ አበባ መጥተው በአንድ አንጋፋ ሆስፒታል የሀሞት ጠጠር እንዳለባቸው እና ቀዶ ህክምና እንደሚደረግላቸው ይነገራቸዋል፡፡ አቶ አስማረ ቀዶ ህክምናውን አጠናቅቀው ወደ በደሌ ቢመለሱም ህመሙ ስለበረታባቸው ተመልሰው መጥተው ምርመራ ቢያደርጉም ምንም የጤና ችግር እንደሌለባቸው በመንገር ይመልሷቸዋል፡፡ ሆኖም ሌላ አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል ምርመራ ሲያደርጉ የሰውነት ክፍላቸው ውስጥ ካቲተር እንዳለ ይነገራቸዋል፡፡ እናም ወደ ሌላ አንጋፋ ሆስፒታል በመሄድ ቀዶ…
