ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ቻይና ቤጂንግ አቅንተዋል፡፡

Abiy Ahmed

በ-እታገኘሁ መኮነን

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ቻይና ቤጂንግ አቅንተው  ከቻይናው አቻቸው ሊ ኪያንግ ጋር  ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም በኢትዮጵያና በቻይና መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊ ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚቻልበትን ሁኔታ አንስተዋል፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ በኢትዮጵያና በቻይና መካከል ያለውን የንግድ አጋርነት ማጠናከር እንደሚያስፈልግም አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡ ከጠቅላይ  ሚኒስቴር ፅ/ቤት  የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ እና ሊ ኪያንግ በተለያዩ ዘርፎች አስራ ሁለት የትብብር ስምምነቶች ተፈራርመዋል፡፡

ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ቤጂንግ ያመሩት በ3ተኛው ቤልት ኤንድ ሮድ ፎረም አለም አቀፍ ትብብር ላይ ለመሳተፍ ነው፡፡