በሀገራዊ ምክክሩ ላይ አዲስ አበባን የወከሉ ወኪሎች የምክክር አጀንዳዎችን ለኮሚሽኑ አስረከቡ
በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በመወከል በሀገራዊ ምክክር የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ሲሳተፉ የቆዩ ተወካዮች ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 27፣ 2017 በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደ የርክክብ ስነ ስርዓት፤ ፤ በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ላይ “ሊመከርባቸው ይገባሉ” ብለው የመረጧቸውን ጉዳዮች ለሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ምክር ቤት አስረከቡ። ተወካዮቹ አጀንዳዎቻቸውን በስምንት ርዕሰ ጉዳዮች በመከፋፈል ያቀረቡ ሲሆን ከእነዚህ ርዕሰ ጉዳዮች መካከል የአዲስ አበባ ባለቤትነት እና አወቃቀር፣ ቋንቋ፣ ታሪክ እና ትርክት፣ የሃገረ መንግስት ግንባታ እና የሃገር አንድነትን፣ የአንድነት እና ብዝሃነትን የሰንደቅ አላማ እና የህገ መንግስት ጉዳዮችን የተመለከቱ ይገኙበታል ተብሏል። አሁን በስራ ላይ ካለውን የኢፌዲሪ ህገ መንግስት…
