በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና የበረሃ አንበጣና ድንበር ተሻጋሪ ተባዮች ስጋት ናቸው ተብሏል።
ይህ ይፋ የተደረገው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የአየር ንብረት ትንበያ እና ትግበራ ማዕከል ICPAC ከኢጋድ አባለ ሀገራት ለተወጣጡ ጋዜጠኞች በሰጠው ስልጠና ላይ ነው። ስልጠናው በዋናነት የበረሃ አንበጣና በሌሎች ድንበር ተሻጋሪ ፀረ ሰብል ተባዮች ላይ ያተኮረ ነው። በተለይ ባለፉት አራት አመታት በቀጠናው ክፉኛ የአንበጣ መንጋ ተከስቶ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን የማዕከሉ ሪፓርት አመላክቷል። በጎረቤት ኬንያ ምዕራባዊ ክፍል በተገባደደው የፈረንጆቹ 2023 ብቻ 5.5 ትሪሊዮን ዶላር የሚገመት እህል በወፎች ወድሟል። ይህም በቶን ሲሰላ 60ቶን ገደማ ነው ተብሏል። በወፎች ከሚጠቁ የሰብል አይነቶች ውስጥ ማሽላ፣ስንዴ፣ሩዝ ጤፍ እና ገብስ በግባር ቀደምትነት ይጠቀሳሉ።የሙቀት መጠን በከፍተኛ ደረጃ መጨመር ለተባዮች መፈልፈል እና መራባት…
