በአማራ ክልል ለተፈጠረው ግጭት ዘላቂ በቂ መፍትሔ ባለመሰጠቱ ምክንያት ከፍተኛ የሆኑ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እየተፈጸሙ ይገኛሉ፡፡ኢሰመጉ
እታገኘሁ መኮነን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ(ኢሰመጉ) ህዳር07/2016“ በአማራ ክልል እየጨመረ የመጣው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ኢሰመጉን በእጅጉ ያሳስቡታል! ” በሚል ባወጣው መግለጫ በአማራ ክልል ለተፈጠረው ግጭት ዘላቂ የሆነ በቂ መፍትሔ ባለመሰጠቱ ምክንያት ከፍተኛ የሆኑ የሰብዓዊ የመብት ጥሰቶች እየተፈጸሙ ይገኛሉ ብሏል፡፡ ኢሰመጉ በአማራ ክልል ውስጥ ያለውን ግጭት አስመልክቶ ለግጭቱ መነሻ የሆኑ ምክንያቶች መታየት ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ በተደጋጋሚ መግለጫዎችን በማውጣት ይህ አለመግባባት ለከፋ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ምክንያት እንዳይሆን ሲያሳስብ እና ሲወተውት ቢቆይም ከመንግስት በኩል ለኢሰመጉ ምክረ ኃሳቦች በቂ ትኩረት ባለመሰጠቱ እና ለግጭቱ ዘላቂ መፍትሔ ባለመቅረቡ ምክንያት መጠነ ሰፊ የሆኑ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች በክልሉ እንዲፈጸሙ ምክንያት ሆኗል ብሏል፡፡ በአማራ ክልል…
