የጋዜጠኛዉ ድምፅ

አንጋፋው ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

አንጋፋው ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

የሀገራችንን ስፖርታዊ እና ታሪካዊ  ክንውኖችን በማቅረብ  በጠቅላላ እውቀቱና መረጃ አያያዙ በርካታ የሚመሰክሩለት አንጋፋው ጋዜጤኛ ገነነ መኩሪያ ሊብሮ ዛሬ አርፏል፡፡ ገነነ የተለያዩ የፅሁፍ ስራዎች በመስራት፣ የራዲዮና ቴሌቭዥን ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት እና በማቅረብ  በማቅረብ  በሚዲያው ላይ ከአርባ አመታት በላይ አገልግሏል። ለአብነት በቀድሞ ዛሚ ኤፍ ኤም፣ በኤፍ ኤም አዲስ ፣ በብስራት ኤፍ ኤም ፣ በአሻም ቴሌቪዥን ላይ የተለያዩ የታሪክና የስፖርት ዝግጅቶችን ባማረና ቀልብን በሚስብ አቀራረብ ሰርቷል። የሀገር ውስጥ ስፖርት ላይ ባለው አስተዋጽኦ ካፍ በ2009 ዓ.ም የ60 ዓመት ጎልደን ኦፍ ሜሪት ሽልማትም ሸልሞታል። ስድስት ጋዜጠኞች ብቻ ያገኙትን ሽልማት በመውሰድ ከምስራቅ አፍሪካ ብቸኛው ነው።  መጋቢት 5/1957 ዓ.ም በይርጋለም የተወለደው ጋዜጠኛ ገነነ ፤ ስፖርትና…
ተጨማሪ ያንብቡ
ጋዜጠኛ አብነት ታምራት መታሰሩ ተሰምቷል።

ጋዜጠኛ አብነት ታምራት መታሰሩ ተሰምቷል።

14/06/2016 ከ1988 ዓ.ም ጀምሮ በበርካታ ጋዜጣና መጽሔቶች በአዘጋጅነት ሲሰራ የቆየው ጋዜጠኛ አብነት ታምራት፣ የከተራ ዕለት በመንግስት የደህንነቶች ኃይሎች መያዙ ተሰምቷል። አብነት በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥሮ መያዙ የተሰማ ሲሆን ትላንትና ሰኞ ፍርድ ቤት አለመቅረቡን እና ወደ አዋሽ አርባ መወሰዱ ታውቋል።
ተጨማሪ ያንብቡ
“በኢትዮጵያ በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች ቁጥር የሚያሳየው፣ የሀገሪቱ ሁኔታ ለመገናኛ ብዙሃን አመቺ አለመሆኑን ነው”ሲፒጄ

“በኢትዮጵያ በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች ቁጥር የሚያሳየው፣ የሀገሪቱ ሁኔታ ለመገናኛ ብዙሃን አመቺ አለመሆኑን ነው”ሲፒጄ

12/06/2016 ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን በማሰር ከአፍሪካ ሃገራት ሶስተኛ ደረጃ መያዟን ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች (ሲፒጄ) ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርቱ አስታውቋል። በአፍሪካ በታሳሪ ጋዜጠኞች ቁጥር ኤርትራ ቀዳሚ ስትሆን ግብፅ ሁለተኛዋ ሃገር ሁናለች፡፡ ሲፒጄ ዓመታዊ ሪፖርቱን ባጠናቀረበት ባለፈው ህዳር ወር መጨረሻ ገደማ፤ በመላው ዓለም የታሰሩ ጋዜጠኞች ብዛት 320 እንደነበር ገልጿል።ከእነዚህም መሃል 5ቱ ሴቶች ሲሆኑ ሁለቱ ኢትዮጵያዊያን ናቸው፡፡ ይህ ቁጥር ድርጅቱ መሰል ሪፖርቶች ማዘጋጀት ከጀመረበት ከ1985 ዓ.ም. ወዲህ በከፍተኛነቱ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚቀመጥ መሆኑንም ጠቁሟል። በአፍሪካ እስካለፈው ህዳር መጨረሻ ድረስ ባለው የአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ፤ ቢያንስ 67 የሚሆኑ ጋዜጠኞች “ከስራቸው ጋር በተያይዘ ለእስር መዳረጋቸውን” ሲፒጄ በሪፖርቱ አመልክቷል።…
ተጨማሪ ያንብቡ
“የዛሬው ቀን ያለትናንት የለም” በሚል መሪ ሃሳብ “ማስታወሻ ሁለት ተካሄደ

“የዛሬው ቀን ያለትናንት የለም” በሚል መሪ ሃሳብ “ማስታወሻ ሁለት ተካሄደ

"የዛሬው ቀን ያለትናንት የለም" በሚል መሪ ሃሳብ "ማስታወሻ ኹለት" ታህሳስ 14 ቀን 2016 በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ተካሂዷል። ማስታወሻ መልቲሚዲያ እና ፕሮሞሽን ጋዜጠኝነት በራሱ ማንነት እንዲሄድ፣ ልምድ እንዲጎለብትና የሀሳብ ልውውጥ እንዲደረግ በተከታታይ መድረኮችን እንደሚያዘጋጅ ይታወቃል። በማስታወሻ መልቲሚዲያና ፕሮሞሽን የተዘጋጀው ይኸው መድረክ፤ ደራሲና ተርጓሚ ሣሕለስላሴ ብርሃነማርያም እና ጋዜጠኛ ግርማ ፍሰሃን(ማንን ምን እንጠይቅልዎ) በዕለቱ የማመስገን እና የመዘከር ስነ ስርዓት ተካሂዷል። በዕለቱ ቀደምቶቹን ከማመስገን ባሻገር የተለያዩ የኪነጥበብ ስራዎች ቀርበዋል። "ማስታወሻ አንድ" ከዚህ ቀደም ደራሲና ጋዜጠኛ ዘነበ ወላን ማመስገንና መዘከሩ የሚታወስ ነው።
ተጨማሪ ያንብቡ
ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ‹‹ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥም ቢሆን በጋዜጠኞችና በመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ላይ የሚኖር ተጠያቂነት ህጋዊ ስርአትን የተከተለ ሊሆን ይገባል›› የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት

ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ‹‹ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥም ቢሆን በጋዜጠኞችና በመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ላይ የሚኖር ተጠያቂነት ህጋዊ ስርአትን የተከተለ ሊሆን ይገባል›› የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት

ጥቅምት 12 ፤2016 ፤አዲስ አበባ )  የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት በሥነ ምግባር የታነጸ በሃላፊነት ስሜት ህዝብን የሚያገለግል ሚዲያ በሀገራችን እንዲጎለብት የሚሰራ ተቋም ሲሆን፤ በሕግ ተመዝግበው ፈቃድ የወሰዱ የህዝብ ፤የንግድ፤ የማህበረሰብ መገናኛ ብዙሃንን፤የበይነ መረብ ሚዲያንና የጋዜጠኞች ሙያ ማህበራትን በአባልነት በማቀፍ የእርስ በእርስ የቁጥጥር ስርዓትን ተግባራዊ እያደረገ የሚገኝ ተቋም ነው፤ምክር ቤታችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማትና ጋዜጠኞች ላይ ከህግ አግባብ ውጪ አስሮ የማቆየትና ለስርጭት የተዘጋጀ የህትመት ውጤትን የማገድ ድርጊቶች እንደተፈፀመባቸውና በዚህም ሳቢያ ተቋማቱ የእለት ተዕለት ስራዎቻቸውን ለመስራት መቸገራቸውን ከደረሱት ሪፖርቶች ተገንዝቧል፡፡በኢትዮጵያ ሕገ መንግስት አንቀፅ 29 ንዑስ አንቀፅ 4 ላይ በግልፅ እንደተመለከተው ‹ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች፤ሃሳቦች፤አመለካከቶች በነፃ መንሸራሸራቸውን ለማረጋገጥ…
ተጨማሪ ያንብቡ
22 ጋዜጠኞች መሞታቸው ተነገረ

22 ጋዜጠኞች መሞታቸው ተነገረ

ጥቅምት 10/2016   ሲፒጄ የእስራኤል እና ሐማስ ግጭት ከጀመረ አንስቶ ቢያንስ 22 ጋዜጠኞች ተገድለዋል አለ። የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ድርጅቱ (ሲፒጄ) ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከተገደሉት ጋዜጠኞች መካከል 18ቱ ፍልስጤማውያን ናቸው ብሏል። የሲፒጄ መግለጫ እንደሚያብራራው 15 ጋዜጠኞች ሕይወታቸውን ያጡት በእስራኤል የአየር ጥቃት ሲሆን ሁለት ጋዜጠኞች ደግሞ በደቡባዊ እስራኤል በሐማስ ጥቃት የተገደሉ ናቸው። ቡድኑ በመግለጫው 8 ጋዜጠኞች ጉዳት እንደደረሰባቸው የገለጸ ሲሆን ሦስት ጋዜጠኞች የደረሱበት እንደማይታወቅ ምናልባትም በእስር ላይ ሊሆኑ ይችላሉ ብሏል። ሲፒጄ ጋዜጠኝነት ሰላማዊ እንቅስቃሴ መሆኑን በመግለጽ ታጣቂዎች ሞያውንና ባለሞያዎቹን ዒላማ ከማድረግ እንዲቆጠቡ አሳስቧል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ