አዲስ ጊዜ

230 Posts
ኢትዮጵያ ለቴሌቪዥን ስርጭት በዓመት 7 ሚሊዮን ዶላር እየከፈለች ነው ተባለ

ኢትዮጵያ ለቴሌቪዥን ስርጭት በዓመት 7 ሚሊዮን ዶላር እየከፈለች ነው ተባለ

የቴሌቪዥን ባለንብረቶች ለሳተላይት ስርጭት የምንከፍለው ዋጋ ጭማሪ አሳስቦናል አሉ፡፡ በዓመት 7 ሚሊዮን ዶላር እየከፈሉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ባለንብረቶች ማህበር በየዓመቱ የሳተላይት ስርጭት የሚከለው ዋጋ ውድነት አሳስቧት ነበር አባላቱ ወደ ኢትዮሳት እንዲገቡ ያደረገው፡፡ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣንም ለእነዚህ የቴሌቭዥን ባለንብረቶች  ስርጭታችሁን በኢትዮ ሳት በኩል ብታደርጉ በየዓመቱ ለሳተላይት የምትከፍሉት ክፍያ ይቀንስላችኋል ብሎ ማበረታቻ ሰጥቶ ነበር፡፡ ይህን ተከትሎ ሰባ የሚሆኑ የቴሌቭዥን ጣቢያዎች  ስርጭታቸውን በኢትዮሳት በኩል ያደረጉ ሲሆን ዓመታዊ ወጪያቸው ግን እንዳልቀነሰላቸው ተናግረዋል፡፡ በአዲስ አበባ በተካሄደው የምስራቅ አፍሪካ ብሮድካስተሮች ጉባኤ ላይ እንደተገለጸው ወጪ ለመቀነስ ብለው ወደ ኢትዮሳት የገቡ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በዓመት ለሳተላይት ስርጭት 7 ሚሊዮን ዶላር እየከፈሉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ…
ተጨማሪ ያንብቡ
የኢትዮጵያ መንግሥት የአሜሪካው አምባሳደር “ሳይጠየቁ ምክር” ሰጥተዋል ሲል ወቀሰ

የኢትዮጵያ መንግሥት የአሜሪካው አምባሳደር “ሳይጠየቁ ምክር” ሰጥተዋል ሲል ወቀሰ

በኢትዮጵያ የአሜሪካው አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ በቅርቡ በሀገሪቱ ያለውን ሁኔታ አስመልክቶ ያሰሙት ንግግር "በደንብ ያልተጤነ" ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ወቀሰ። አምባሰደር ማሲንግ ከጥቂት ቀናት በፊት "ፖሊሲ ስፒች ኦን ሂዩማን ራይትስ ኤንድ ዳያሎግ" የተሰኘ ንግግር አሰምተው ነበር። ማሲንጋ በንግግራቸው መሠረተ ልማቶችን ዒላማ ያደረጉ ጥቃቶች እንዲቆሙ፤ ያልተገደበ ሰብአዊ አቅርቦት እንዲኖር እና ለዚህም መነሻ የሚሆን ጊዜያዊ አገር አቀፍ የተኩስ አቁም አንዲደረግ አሳስበው ነበር። ማሲንጋ  በንግግራቸው ሽፍቶች፣ ታጣቂ ቡድኖችና አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በህይወት የመኖር እና የመከባበር መብቶች ላይ ጥሰት መፈፀማቸው የሕግ ሂደትንና የሕግ የበላይነት አለማክበርን የሚያሳይ ነው ብለዋል። በጦርነት እና ግጭት ጊዜም ቢሆን “የሰብዓዊ መብት እና ሰብዓዊ ክብር”…
ተጨማሪ ያንብቡ
የሴት ልጅ ግርዛትን የተመለከተው አወዛጋቢው የኢትዮጵያ ዑለማዎች ውሳኔ

የሴት ልጅ ግርዛትን የተመለከተው አወዛጋቢው የኢትዮጵያ ዑለማዎች ውሳኔ

የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ የዑለማ ጉባዔ፣ የ2ኛ ዓመት መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔን በማስመልከት የወጣው መግለጫ በማኅበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ሆኗል። የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ይፋዊ የፌስቡክ ገጽ ላይ ጥር 22 ቀን፣ 2016 ዓ. ም. ባወጣው መግለጫ ላይ የሴት ልጅ ግርዛትን በተመለከተ በቁጥር 12 እና 13 ላይ የሰፈረው ውሳኔ ከሴቶች መብት እንዲሁም ከኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት አንጻር ተቃርኖ እንዳለው እንደ “አዲስ ፓወር ሃውስ’’ እና “አርቲክል 35” ያሉ በሴቶች መብት ላይ የሚሠሩ ንቅናቄዎች በማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻቸው ድምጻቸውን እያስተጋቡ ነው። በመግለጫው ላይ በቁጥር 12 እና 13 የሰፈሩት ውሳኔዎች እንደሚከተለው ተቀምጠዋል። እነዚህንና ሌሎች በመግለጫው የተካተቱ “ውሳኔዎችና ፈትዋዎችን የእስልምና ጉዳዮች…
ተጨማሪ ያንብቡ
“ሁለት ጊዜ ምዘና ያላለፉ ሰራተኞች  ይሰናበታሉ፡፡”አዲሱ የሰራተኞች ረቂቅ አዋጅ

“ሁለት ጊዜ ምዘና ያላለፉ ሰራተኞች  ይሰናበታሉ፡፡”አዲሱ የሰራተኞች ረቂቅ አዋጅ

አዲሱ የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች ረቂቅ አዋጅ ትናንት ማክሰኞ ግንቦት 6/2016 ዓ.ም. ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ውይይት ተካሄደበት።  17 ክፍሎች እና በ160 አንቀጾችየያዘው ይህ ረቂቅ  አሁን በስራ ላይ ካለው አዋጅ አንጻር ዝርዝር ጉዳዮችን የያዘ እና ከዚህ ቀደም በሌላ አዋጅ ይሸፈኑ የነበሩ ጉዳዮችን ያካተተ ነው ተብሏል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከታህሳስ ወር ጀምሮ ነባር ሰራተኞች ላይ አዲስ ድልድል ሲያከናውን በመስፈርትነት የተጠቀማቸው የምዘና እና ሕብረ ብሔራዊነት እና አካታችነት ጉዳይም በረቂቁ ተካትተዋል። አዲስ አዋጅ ሲዘጋጅ ለማሳካት ከታቀዱ ዓላማዎች ውስጥ አንዱ “በመንግሥት መስሪያ ቤት የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለማስፈፀም ብቃት ያላቸውን ባለሙያዎች ለማግኘት እና በሥራ ላይ ያሉትንም ለማቆየት” የሚለው አንዱ እንደሆነ በረቂቁ…
ተጨማሪ ያንብቡ
ኢትዮጵያ የላሙ ወደብን መጠቀም ጀመረች

ኢትዮጵያ የላሙ ወደብን መጠቀም ጀመረች

ኬንያ፣ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን የላሙ ወደብን ለማልማት እና ለመጠቀም በ2001 ዓ.ም በወቅቱ የኬንያ ፕሬዝዳንት፣ ሞ ኪባኪ፣ በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እና በደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት አማካኝነት ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡ ኬንያ ይህን ፕሮጀክት በማልማት ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን እንዲጠቀሙበት ፍላጎት ያላት ቢሆንም ኢትዮጵያ እስካሁን ፍላጎት እንዳልነበራት ተገልጿል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መንግስት ኢትዮጵያ ተጨማሪ የገቢ ወጪ ንግድ አማራጭ ወደብ እንዲኖራት የተለያዩ ጥረቶችን በማድረግ ላይ ሲሆን የላሙ ወደብን አንዱ አማራጭ አድርጎ ለመጠቀም መወሰኑ ከወራት በፊት መግለጻቸው አይዘነጋም፡፡ ይህ ስምምነት ከተፈረመ ከ15 ዓመታት በኋላ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የላሙ ወደብን መጠቀም ጀምራለች፡፡ “ዓባይ” የተሰኘችው የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ…
ተጨማሪ ያንብቡ
አውሮፓዊያን እና አሜሪካ ተባብረው እያስፈራሩኝ ነው ስትል ኢትዮጵያ ወቀሰች፡፡

አውሮፓዊያን እና አሜሪካ ተባብረው እያስፈራሩኝ ነው ስትል ኢትዮጵያ ወቀሰች፡፡

ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ 18 ምዕራባውያን ሀገራት  እና ኢምቢሲዎች እና የአሜሪካ ኤምባሲ ‘የዓለም የፕሬስ ነጻነት ቀንን’ አስመልክተው ባሳለፍነው ሳምንት ባወጡት የጋራ መግለጫ የኢትዮጵያን የጋዜጠኞች አያያዝ መተቸታቸው ይታወሳል፡፡ አሜሪካ፣ የአውሮፓ ህብረት፣ ብሪታንያ፣ ጀርመን፣ ስዊድን፣ ቤልጂየም፣ ኖርዌይ፣ ስፔን፣ ኔዘርላንድ እና ሌሎች የአውሮፓ ህብረት ሃገራት በጋራ ባወጡት መግለጫ  ኢትዮጵያ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን እንድታከብር ጠይቀዋል፡፡ ሀገራቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ጋዜጠኞች ስራቸውን በመስራታቸው “ማስፈራሪያ እና እስር ይደርሰባቸዋል” ሲሉ በመግለጫቸው ላይ ጠቅሰውም ነበር። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር  ቃል አቀባይ አቶ ነብዩ ተድላ በዚህ ዙሪያ ለጋዜጠኞች  በሰጡት መግለጫ  ምዕራባዊን ሀገራት በቡድን መግለጫ በማውጣት  ሊያስፈራሩን ሞክረዋል   ሲሉ ተናግረዋል፡፡ “ኢትዮጵያ መግለጫውን ካወጡት እያንዳንዳቸው ሀገራት ጋር…
ተጨማሪ ያንብቡ
መንግሥት የሪል ስቴት ንብረት ታክስና የተሽከርካሪ ዝውውር ላይ ታክስ ለመጣል አቀደ

መንግሥት የሪል ስቴት ንብረት ታክስና የተሽከርካሪ ዝውውር ላይ ታክስ ለመጣል አቀደ

መንግሥት የአገሪቱን የታክስ ገቢ ለማሳደግ የሪል ስቴት ንብረት ታክስና የሞተር ተሽከርካሪ ዝውውር ታክስ ለመጣል ማቀዱን ሪፖርተር ዘግቧል፡፡ መንግሥት ሁለቱንም አዲስ ዓይነት ታክሶች ከዘንድሮ ጀምሮ እስከሚቀጥለው ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ ለመጣል ያቀደ ሲሆን፣ ይህንን ዕቅዱንም በሁለተኛው አገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ሰነድ ውስጥ እንደተካተተ ሪፖርተር ከሰነዱ ለመረዳት ችያለሁ ብሏል፡፡ የታቀደው የሞተር ተሽከርካሪ ዝውውር ታክስ በአገሪቱ ውስጥ ባሉ ሁሉም ተሽከርካሪዎች ላይ የሚተገበር እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል ይላል ዘገባው።. ታክሱ በዓመት የሚከፈል ሲሆን፣ የተሽከርካሪ ባለቤቶች ለተሽከርካሪዎቻቸው የገዙትን ኢንሹራንስ በሚያሳድሱበት ወቅት አብሮ እንደሚሰበሰብ የአገሪቱ መንግሥት አስታውቋል ብሏል ሪፖርተር። የፌዴራል መንግሥት የተሽከርካሪ ዝውውር ታክስ የመጣል ሥልጣንን በሕግ በማቋቋም የታክስ ገቢውን የመሰብሰብና የመጠቀም ኃላፊነቶችን…
ተጨማሪ ያንብቡ
‹‹በሐሰተኛ ሰነድ በሚኖሩና በሚሸጡ የውጭ አገር ዜጎች ላይ ዕርምጃ መውሰድ አልቻልኩም›› የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

‹‹በሐሰተኛ ሰነድ በሚኖሩና በሚሸጡ የውጭ አገር ዜጎች ላይ ዕርምጃ መውሰድ አልቻልኩም›› የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በሕገወጥ መንገድና በሐሰተኛ ሰነድ አገር ውስጥ የሚገኙ የውጭ አገር ዜጎችን በፍርድ ቤት በመክሰስ ዕርምጃ እንዲወሰድባቸው ሲሞከር፣ በዋስ እየተለቀቁ መቸገሩን አስታውቋል ሲል ሪፖርተር ዘግቧል፡፡ እንደ ሪፖተር ዘገባ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ሚያዝያ 18 ቀን 2016 ዓ.ም. የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን ባቀረበበት ወቅት የመኖሪያ ፈቃድ የጨረሱ የውጭ አገር ዜጎች ላይ ሕጋዊ ዕርምጃ ከመውሰድ አንፃር ምን እየተሠራ እንደሆነ ከሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጥያቄ ቀርቦለታል፡፡  ቋሚ ኮሚቴው የውጭ አገር ዜጎች ፈቃድ በተፈቀደላቸው የመኖሪያ የጊዜ ገደብ ብቻ እንዲቆዩ ከማድረግ አንፃር አፈጻጸሙ 36 በመቶ ብቻ መሆኑን በሪፖርቱ እንደተመለከተ ዘገባው አስነብቧል፡፡ ተቋሙን እየመሩ ያሉት አመራሮች ወደ ኃላፊነት ሲመጡ ባደረጉት…
ተጨማሪ ያንብቡ
በኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ መንገደኞች ቤተሰቦች ቦይንግ በወንጀል እንዲከሰስ ጠየቁ

በኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ መንገደኞች ቤተሰቦች ቦይንግ በወንጀል እንዲከሰስ ጠየቁ

በኢትዮጵያ አየር መንገድ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን ከአምስት ዓመት በፊት ሕይወታቸውን ያጡ መንገደኞች ቤተሰቦች ለአደጋው መንስዔ የሆነው የአውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ ላይ የወንጀል ክስ እንዲመሠረት የአሜሪካ የፍትህ መሥሪያ ቤትን ጠየቁ። የመንገደኞቹ ቤተሰቦች በዋሽንግተን ከአሜሪካ የፍትህ ባለሥልጣናት ጋር ሚያዝያ 16/ 2016 ዓ.ም በተነጋገሩበት ወቅት የአሜሪካው ኩባንያ ቦይንግ ለፍርድ እንዲቀርብ ጠይቀዋል። የተጎጂዎች ቤተሰቦች እና ተወካይ ጠበቆቻቸው ኩባንያው የሚያመርታቸውን አውሮፕላን ምርቶች ደኅንነት እና ጥራት ለማስጠበቅ ከሦስት ዓመት በፊት ከአሜሪካ የፍትህ ሚኒስቴር ጋር የገባውን የቁጥጥር መርሃ ግብር ስምምነት ጥሷል ብለዋል። የ157 ሰዎችን ሕይወት ከቀጠፈው ከኢትዮጵያው አደጋ በተጨማሪ ለ189 ሰዎች ሕይወት ማለፍ ምክንያት በሆነው የኢንዶኔዥያ አየር መንገድ አደጋ ቤተሰቦቻቸውን ያጡ ቦይንግ በወንጀል…
ተጨማሪ ያንብቡ
ሴቶች በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ውስጥ እንዴት ሊሳተፉ ይችላሉ?

ሴቶች በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ውስጥ እንዴት ሊሳተፉ ይችላሉ?

በኢትዮጵያ ሴቶች ከአጠቃላይ ማህበረሰቡ ከ50 በመቶ በላይ እንደሚሸፍኑ መረጃዎች ቢያመለክቱም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ያላቸው ተሳትፎ ግን ከቁጥራቸው አንፃር እዚህ ግባ የማይባል እንደሆነ ነው ጥናታዊ መረጃዎች የሚያመለክቱት፡፡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ይህንን ሁኔታ ለመቀየር ሲያስተባብር በቆየው የምክክር ሂደት ውስጥ የሴቶችን ተሳትፎ በሚገባቸው ልክ ለማድረግ ተጨባጭ ስራዎችን ሰርቷል፡፡ የእስካሁኑ የኮሚሽኑ ጥረት እንዳለ ሆኖ ኮሚሽኑ በቅርቡ በሚያስተባብረው የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት የሴቶችን ተሳትፎ ከመቼውም ጊዜ በላይ ለማሻሻል ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው፡፡ ታዲያ ሴቶች በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ውስጥ እንዴት ሊሳተፉ ይችላሉ? 1. የማህበረሰብ ክፍሎችን በመወከል በኮሚሽኑ ከተለዩት ባለድርሻ አካላት መካከል የማህበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሽ ባለድርሻ አካል ናቸው፡፡ ከእነዚህ የማህበረሰብ ክፍሎች አንዱ ሴቶች…
ተጨማሪ ያንብቡ