“ሁለት ጊዜ ምዘና ያላለፉ ሰራተኞች ይሰናበታሉ፡፡”አዲሱ የሰራተኞች ረቂቅ አዋጅ
አዲሱ የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች ረቂቅ አዋጅ ትናንት ማክሰኞ ግንቦት 6/2016 ዓ.ም. ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ውይይት ተካሄደበት። 17 ክፍሎች እና በ160 አንቀጾችየያዘው ይህ ረቂቅ አሁን በስራ ላይ ካለው አዋጅ አንጻር ዝርዝር ጉዳዮችን የያዘ እና ከዚህ ቀደም በሌላ አዋጅ ይሸፈኑ የነበሩ ጉዳዮችን ያካተተ ነው ተብሏል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከታህሳስ ወር ጀምሮ ነባር ሰራተኞች ላይ አዲስ ድልድል ሲያከናውን በመስፈርትነት የተጠቀማቸው የምዘና እና ሕብረ ብሔራዊነት እና አካታችነት ጉዳይም በረቂቁ ተካትተዋል። አዲስ አዋጅ ሲዘጋጅ ለማሳካት ከታቀዱ ዓላማዎች ውስጥ አንዱ “በመንግሥት መስሪያ ቤት የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለማስፈፀም ብቃት ያላቸውን ባለሙያዎች ለማግኘት እና በሥራ ላይ ያሉትንም ለማቆየት” የሚለው አንዱ እንደሆነ በረቂቁ…
