የሴት ልጅ ግርዛትን የተመለከተው አወዛጋቢው የኢትዮጵያ ዑለማዎች ውሳኔ
የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ የዑለማ ጉባዔ፣ የ2ኛ ዓመት መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔን በማስመልከት የወጣው መግለጫ በማኅበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ሆኗል። የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ይፋዊ የፌስቡክ ገጽ ላይ ጥር 22 ቀን፣ 2016 ዓ. ም. ባወጣው መግለጫ ላይ የሴት ልጅ ግርዛትን በተመለከተ በቁጥር 12 እና 13 ላይ የሰፈረው ውሳኔ ከሴቶች መብት እንዲሁም ከኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት አንጻር ተቃርኖ እንዳለው እንደ “አዲስ ፓወር ሃውስ’’ እና “አርቲክል 35” ያሉ በሴቶች መብት ላይ የሚሠሩ ንቅናቄዎች በማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻቸው ድምጻቸውን እያስተጋቡ ነው። በመግለጫው ላይ በቁጥር 12 እና 13 የሰፈሩት ውሳኔዎች እንደሚከተለው ተቀምጠዋል። እነዚህንና ሌሎች በመግለጫው የተካተቱ “ውሳኔዎችና ፈትዋዎችን የእስልምና ጉዳዮች…
