ሀገርኛ

የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ አገልግሎትከፍተኛ አመራሮች መታሰራቸው ተሰማ

የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ አገልግሎትከፍተኛ አመራሮች መታሰራቸው ተሰማ

ጥቅምት 07/2016 የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ታምሩ ገምበታን ጨምሮ በቁጥር ለጊዜው ያልታወቁ ሰዎች በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው መታሰራቸው ተሰማ። ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሰሞኑን ሲሆን አቶ ታምሩ ገምበታ ግን ጥቅምት 5 ቀን 2016 ዓ.ም. መሆኑ ተገልጿል። የምክትል ዳይሬክተሩ ቤት በፍርድ ቤት የብርበራ ፈቃድ መፈተሹንና ዛሬ ጥቅምት 7 ቀን 2015 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ሊቀርቡ እንደሚችሉ ተጠቁሟል፡፡ የመንግሥት አስተዳደር ለውጥ ከተደረገ ጀምሮ የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ አገልግሎት ተቋም ውስጥ የተለያዩ ለውጦች (ሪፎርም) የተደረገ ቢሆንም፣ አንዳንድ የተቋሙ ሠራተኞች በድለላ ሥራ ከተሰማሩ አካላት ጋር በመመሳጠር የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው በቁጥጥር ሥር ውለው በምርመራ ላይ እንዳሉ ይታወቃል። አገልግሎቱን…
ተጨማሪ ያንብቡ
ደጃዝማች ባልቻ አባነፍሶ እና የቅዱስ ጳውሎስ ሪፈራል ሆስፒታል ላይ ፍርድ ቤት የቅጣት ውሳኔ አስተላለፈ

ደጃዝማች ባልቻ አባነፍሶ እና የቅዱስ ጳውሎስ ሪፈራል ሆስፒታል ላይ ፍርድ ቤት የቅጣት ውሳኔ አስተላለፈ

በ-እታገኘሁ መኮነን በተደጋገሚ የህክምና ስህተት አራት ጊዜ ቀዶ ህክምና ለማድረግ የተገደዱት እና ሁለት ጊዜ ባዕድ ነገር የሰውነት ክፍላቸው ውስጥ የተረሳባቸው ግለሰብ የሁለት ሚሊዮን ብር የካሳ ክፍያ አገኙ፡፡ ግለሰቡ አቶ አስማረ አለሙ ይባላሉ፡፡ የኢሊባቦር በደሌ ነዋሪ ናቸው፡፡ 2006 ላይ ለህክምና ወደ አዲስ አበባ መጥተው በአንድ አንጋፋ ሆስፒታል የሀሞት ጠጠር እንዳለባቸው እና ቀዶ ህክምና እንደሚደረግላቸው ይነገራቸዋል፡፡ አቶ አስማረ ቀዶ ህክምናውን አጠናቅቀው ወደ በደሌ ቢመለሱም ህመሙ ስለበረታባቸው ተመልሰው መጥተው ምርመራ ቢያደርጉም ምንም የጤና ችግር እንደሌለባቸው በመንገር ይመልሷቸዋል፡፡ ሆኖም ሌላ አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል ምርመራ ሲያደርጉ የሰውነት ክፍላቸው ውስጥ ካቲተር እንዳለ ይነገራቸዋል፡፡ እናም ወደ ሌላ አንጋፋ ሆስፒታል በመሄድ ቀዶ…
ተጨማሪ ያንብቡ
ምክር ቤቱ ከሩሲያ፣ ሊባኖስና ፓኪስታን ጋር የተያያዙ አዋጆች ላይ መከረ

ምክር ቤቱ ከሩሲያ፣ ሊባኖስና ፓኪስታን ጋር የተያያዙ አዋጆች ላይ መከረ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባው፣ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል በሁለትዮሽ ወታደራዊ ቴክኒካዊ ትብብር ወቅት የተገኙ የአዕምሯዊ የፈጠራ ሥራ ውጤቶችና ንብረቶች የጋራ ጥበቃ ስምምነት ማጽደቂያ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለውጭ ግንኙነትና ለሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቷል፡፡ስምምነቱ የሁለቱን አገራት ወዳጅነት የበለጠ ለማጠናከር የተፈረመ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ በሁለትዮሽ ወታደራዊ የቴክኒካል ትብብር ሂደቱ ውስጥ በአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ መስክ የተሻለ የጋራ መግባባትና ትብብር እንዲኖር ለማድረግ የሚያግዝ ነው ተብሏል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ምክር ቤቱ በዛሬው ውሎ በኢትዮጵያና በሊባኖስ መንግሥታት መካከል በሥራ ስምሪት ዘርፍ የተፈረመውን ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ለሰው…
ተጨማሪ ያንብቡ
የሐይማኖት ተቋማት መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ምስረታ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ

የሐይማኖት ተቋማት መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ምስረታ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ

በአሸናፊ አሰበ ጥቅምት 3 ይመሰረታል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው የሐይማኖት ተቋማት መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ምስረታ የሚያቋቁሙት አካላት በምስረታው ሂደት ላይ አንዳንድ ስራዎች ቀርተውናል በማለታቸው ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ደሴ ከፍያለው ለአዲስ ጊዜ ገለጹ፡፡ ምክር ቤቱ የእርስ በእርስ ቁጥጥርን በሐይማኖት መገናኛ ብዙሀን መካከል ከማጠናከሩም ባሻገር እርስ በእርስ ለመተራረም፣ ዘርፉን ለማሳደግ፣ በጋራ ጉዳዮች አብሮ ለመስራት እና ለመተባበር ታሳቢ ተደርጎ እንደሚቋቋም የገለጹት ዳይሬክተሩ ነገር ግን ምክር ቤቱን የማቋቋም ስልጣን የመገናኛ ብዙሀን መስሪያ ቤት አለመሆኑና ይህን የማድረግ ሀላፊነት ሙሉ በሙሉ የሃይማኖት ተቋማቱ የሚዲያ ኃላፊዎች እንደሆነ አቶ ደሴ አያይዘው ገልጸዋል፡፡ የመገናኛ ብዙሃን የእርስ በእርስ ቁጥጥር ማለት…
ተጨማሪ ያንብቡ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ቻይና ቤጂንግ አቅንተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ቻይና ቤጂንግ አቅንተዋል፡፡

በ-እታገኘሁ መኮነን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ቻይና ቤጂንግ አቅንተው  ከቻይናው አቻቸው ሊ ኪያንግ ጋር  ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም በኢትዮጵያና በቻይና መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊ ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚቻልበትን ሁኔታ አንስተዋል፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ በኢትዮጵያና በቻይና መካከል ያለውን የንግድ አጋርነት ማጠናከር እንደሚያስፈልግም አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡ ከጠቅላይ  ሚኒስቴር ፅ/ቤት  የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ እና ሊ ኪያንግ በተለያዩ ዘርፎች አስራ ሁለት የትብብር ስምምነቶች ተፈራርመዋል፡፡ ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ቤጂንግ ያመሩት በ3ተኛው ቤልት ኤንድ ሮድ ፎረም አለም አቀፍ ትብብር ላይ ለመሳተፍ ነው፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
‹‹ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ላይ የሚደርሰው ግፍ’ና መከራ ሃይማኖትን የሚያጠፋ የሃገር መሠረት የሆነውን እሴት የሚንድ ነው ›› – አቡነ ማትያስ

‹‹ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ላይ የሚደርሰው ግፍ’ና መከራ ሃይማኖትን የሚያጠፋ የሃገር መሠረት የሆነውን እሴት የሚንድ ነው ›› – አቡነ ማትያስ

 በዳዊት ታደሰ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቤተክርስቲያኗ ለ42ኛ ጊዜ የምታካሂደውን አመታዊ ዓለማቀፍ ጉባኤ ተከትሎ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ‹‹ በቤተክርስቲያኗ፣ ምዕመኗ እንዲሁም አገልጋይ ካህናቶቿ ላይ የሚደረው ግፍና መከራ ሄዶ ሄዶ ሃይማኖትን የሚያጠፋ ነው ›› ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ ‹‹ በቤተክርስቲያኗ ምዕመናን እና አገልጋይ ካህናቶቿ ላይ የሚደርሰው ሞት፣ ስደት፣ መፈናቀል እና እንግልት ኢትዮጵያ አለኝ የምትለውን እሴት በማጥፋት ሃገሩን፣ ባህሉን፣ እሴቱን በጥቅሉ ማነንቱን የማያውቅ ትውልድ እንዲፈጠር ያደርጋል ›› ሲሉም አክለዋል፡፡ ድርጊቱ ሃገሩን ባህሉን እሴቱን በጥቅሉ ኢትዮጵያዊ ማንነውቱን የማያውቅ ትውልድ እንደሚፈጠር የሚናገሩት አቡነ ማትያስ ይህ አይነቱ ትውልድ ከመፈጠሩ አስቀድሞ በጥንካሬ መስራት እንደሚያስፈልግም መክረዋል። በምዕመናን ህልውና ላይ…
ተጨማሪ ያንብቡ