የመንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት 2ኛው ዙር ድርድር ያለ ስምምነት አበቃ
በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መካከል በታንዛኒያዋ ዳሬሰላም ከተማ ለቀናት ሲካሄድ የነበረው ድርድር ያለውጤት መበተኑን መንግሥት አስታወቀ። ይህንን ያሳወቁት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ እና መንግሥትን ወክልው በድርድሩ ላይ ተሳታፊ የነበሩት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ናቸው። አምባሳደር ሬድዋን በኤክስ (የቀድሞው ትዊተር) ላይ ማክሰኞ ኅዳር 11/2016 ዓ.ም. ምሽት ላይ ባሰራጩት መልዕክት እንዳሉት ሲካሄድ የሰነበተው ድርድር ካለስምምነት በመጠናቀቁ የኢትዮጵያ መንግሥት ማዘኑን አመልክተዋል። ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ወር ላይ በታንዛኒያ የመዝናኛ ደሴት ዛንዚባር ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በመንግሥት እና በአማጺው መካከል በተመሳሳይ ለቀናት የቆየ ድርድር ሲካሄድ ቆይቶ ያለስምምነት መጠናቀቁ ይታወሳል። ሁለተኛው ዙር ድርድር ሁለት ሳምንት ለሚጠጋ ጊዜ በታንዛኒያ ዋና…
