አዲስ ዜና

የመንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት 2ኛው ዙር ድርድር ያለ ስምምነት  አበቃ

የመንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት 2ኛው ዙር ድርድር ያለ ስምምነት አበቃ

በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መካከል በታንዛኒያዋ ዳሬሰላም ከተማ ለቀናት ሲካሄድ የነበረው ድርድር ያለውጤት መበተኑን መንግሥት አስታወቀ። ይህንን ያሳወቁት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ እና መንግሥትን ወክልው በድርድሩ ላይ ተሳታፊ የነበሩት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ናቸው። አምባሳደር ሬድዋን በኤክስ (የቀድሞው ትዊተር) ላይ ማክሰኞ ኅዳር 11/2016 ዓ.ም. ምሽት ላይ ባሰራጩት መልዕክት እንዳሉት ሲካሄድ የሰነበተው ድርድር ካለስምምነት በመጠናቀቁ የኢትዮጵያ መንግሥት ማዘኑን አመልክተዋል። ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ወር ላይ በታንዛኒያ የመዝናኛ ደሴት ዛንዚባር ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በመንግሥት እና በአማጺው መካከል በተመሳሳይ ለቀናት የቆየ ድርድር ሲካሄድ ቆይቶ ያለስምምነት መጠናቀቁ ይታወሳል። ሁለተኛው ዙር ድርድር ሁለት ሳምንት ለሚጠጋ ጊዜ በታንዛኒያ ዋና…
ተጨማሪ ያንብቡ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ  አሁን በውስጥ አቅም የሚሰሩ የተወሰኑ  ሥራዎችን ለ3ተኛ ወገን በማስተላለፍ  ለማሰራት ወሰኗል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ  አሁን በውስጥ አቅም የሚሰሩ የተወሰኑ  ሥራዎችን ለ3ተኛ ወገን በማስተላለፍ  ለማሰራት ወሰኗል፡፡

ውሳኔው የተወሰነው ዛሬ በተካሄደው የካቢኔው የ3ኛ ዓመት 5ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ሲሆን ውሳኔውን ለመወሰን የሚያስችል በቂ ጥናት እና ዝግጅት መደረጉ ተነግሯል፡፡ለሦስተኛ ወገን የሚተላለፉት ሥራዎች ግን ተለይተው አልተገለፁም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ካቢኔው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን በማዕከል ያለውን የሰራተኛ ቁጥር በመቀነስ ወደ ወረዳና ሌሎች ተቋማት ምደባ እንደሚደረግ ተነግሯል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
በአማራ ክልል ለተፈጠረው ግጭት ዘላቂ በቂ መፍትሔ ባለመሰጠቱ ምክንያት ከፍተኛ የሆኑ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እየተፈጸሙ ይገኛሉ፡፡ኢሰመጉ

በአማራ ክልል ለተፈጠረው ግጭት ዘላቂ በቂ መፍትሔ ባለመሰጠቱ ምክንያት ከፍተኛ የሆኑ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እየተፈጸሙ ይገኛሉ፡፡ኢሰመጉ

እታገኘሁ መኮነን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ(ኢሰመጉ) ህዳር07/2016“ በአማራ ክልል እየጨመረ የመጣው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ኢሰመጉን በእጅጉ ያሳስቡታል! ” በሚል ባወጣው መግለጫ በአማራ ክልል ለተፈጠረው ግጭት  ዘላቂ የሆነ በቂ መፍትሔ ባለመሰጠቱ ምክንያት ከፍተኛ የሆኑ የሰብዓዊ የመብት ጥሰቶች እየተፈጸሙ ይገኛሉ ብሏል፡፡ ኢሰመጉ በአማራ ክልል ውስጥ ያለውን ግጭት አስመልክቶ ለግጭቱ መነሻ የሆኑ ምክንያቶች መታየት ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ በተደጋጋሚ መግለጫዎችን በማውጣት ይህ አለመግባባት ለከፋ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ምክንያት እንዳይሆን ሲያሳስብ እና ሲወተውት ቢቆይም ከመንግስት በኩል ለኢሰመጉ ምክረ ኃሳቦች በቂ ትኩረት ባለመሰጠቱ እና ለግጭቱ ዘላቂ መፍትሔ ባለመቅረቡ ምክንያት መጠነ ሰፊ የሆኑ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች በክልሉ እንዲፈጸሙ ምክንያት ሆኗል ብሏል፡፡ በአማራ ክልል…
ተጨማሪ ያንብቡ
አንቶኒ ብሊንከን ከጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር በስልክ ተወያዩ 

አንቶኒ ብሊንከን ከጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር በስልክ ተወያዩ 

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር የስልክ ውይይት ማድረጋቸው ተነግሯል። በውይይታቸው ላይ በቀጣይ ወር በኢትዮጵያ ተቋርጦ ስለነበረው እና ዳግም ሊጀመር ስለታሰበው የምግብ እርዳታ አቅርቦት መምከራቸውን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ቢሮ ገልጿል። ብሊንከን የኢትዮጵያ መንግስት እና የሰብአዊ ዕርዳታ አጋሮች ለከፋ የምግብ ዋስትና ችግር ለተጋለጡ ወገኖች የምግብ እርዳታ መድረሱን ለማረጋገጥ ያደረጉትን ማሻሻያ አድንቀዋል ተብሏል። አንቶኒ ብሊንከን እና ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ በሰሜን ኢትዮጵያ ሰላምን ለማጠናከር በሚደረገው ጥረት እና የቀጠናዊ ትብብር አስፈላጊነት ላይ ተወያይተዋል ሲልም የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ ቢሮ ጨምሮ አስታውቋል። በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶች እንዳሳሰባቸው…
ተጨማሪ ያንብቡ
ኢሰመኮ ዓለም አቀፍ ለጋሽ ድርጅቶች እርዳታ ለመቀጠል መወሰናቸውን አደነቀ

ኢሰመኮ ዓለም አቀፍ ለጋሽ ድርጅቶች እርዳታ ለመቀጠል መወሰናቸውን አደነቀ

ዳዊት ታደሰ የኢትዮጵያ ሰበአዊ መብቶች ኮሚሽን ህዳር 07 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ የአሜሪካ መንግስት የዓለም አቀፍ ልማት ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስ ኤድ) እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዓለም የምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ አቋርጠውት የነበረውን የምግብ እርዳታ መልሰው ለመጀመር መወሰናቸው የሚወደስ ነው ብሏል፡፡ ኢሰመኮ በመግለጫው፣ በትግራይ ክልል ከባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ጀምሮ በኢትዮጵያ ደረጃ ደግሞ ከሰኔ ወር ጀምሮ የተቋረጠውን የምግብ እህል እርዳታ ተከትሎ ስለተፈጠረው ሁኔታ ክትትል ሲያደርግ እንደነበር ዘርዝሯል፡፡ ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ፍልሰተኞች በተለይ ደግሞ ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት ጋር ለመድረስ እንዲቻል አስተዳደራዊ እርምጃዎችን ጨምሮ ሌሎች የማስተባበር ስራዎች በፍጥነት እንዲከወኑ ሲወተውት መቆየቱን ያስታወሰው ኮሚሽኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት…
ተጨማሪ ያንብቡ
ዩ.ኤስ.ኤድ ያቋረጠውን ርዳታ ሊጀምር ነው

ዩ.ኤስ.ኤድ ያቋረጠውን ርዳታ ሊጀምር ነው

ዩኤስኤድ ከወራት በፊት አቋርጦት የነበረውን የምግብ እርዳታ አቅርቦት ከቀጣይ ወር ጀምሮ በመላ ኢትዮጵያ እንደሚጀምር ማስታወቁ ተዘግቧል።በኢትዮጵያ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለተጎጂዎች ተብሎ የሚቀርብ እርዳታ ላልታለመለት አላማ እየዋለ መሆኑ በመረጋገጡ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ዩኤስኤድ በኢትዮጵያ የሚያካሂደውን የእርዳታ አቅርቦት ማቋረጡ ይታወሳል። ዩ.ኤስ.ኤድ በመላ ሀገሪቱ ለአንድ አመት ያክል የእርዳታ ስርጭቱን በማካሄድ ለመሞከር ማቀዱን አስታውቋል ያለው የሮይተርስ ዘገባ በዚህ የሙከራ ጊዜ የምግብ እርዳታውን አቅርቦት ለሚገባቸው ተረጂዎች መዳረሱን ክትትል እንደሚያደርግ እና ምርምራ እንደሚያከናውን መግለጹን አመላክቷል። የረድኤት ድርጅቱ የምግብ አቅርቦቱን የሚጀምረው ለበርካታ ወራት ከመንግስት ጋር ዲፕሎማሲያዊ ድርድሮች ከተከናወኑ በኋላ መሆኑን የጠቆመው ዘገባው የኢትዮጵያ መንግስት እና አጋር አካላት ከእርዳታ እደላ ጋር በተያያዘ እጅግ አስፈላጊ…
ተጨማሪ ያንብቡ