ኢሰመኮ ሰሞኑን ያወጣሁትን መግለጫ ላይ ማስተካከያ አደርጋለሁ ብሏል፡፡
አርብ ጥቅምት 15 /2016 ኢሰመኮ ሰሞኑን ባወጣው ኹለተኛው አገር ዓቀፍ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ሪፖርት ትግራይን አስመልክቶ የተሳሳተ መረጃ ማካተቱን ትናንት ምሽት ባወጣው እርማት አስታውቋል። ኮሚሽኑ በሪፖርቱ፣ በሰሜኑ ጦርነት የተፈናቀሉ በርካታ ሰዎች ወደቀያቸው እንደተመለሱና ጅምሩ መልካም ርምጃ እንደኾነ ገልጦ ነበር። ለሪፖርቱ የተሠራው ጥናት ትግራይን አያካትትም ነበር ያለው ኮሚሽኑ፣ የተሳሳተውን መረጃ ከክልሉ አስተዳደር ጋር በመተባበር እንደሚያጣራው ገልጧል።
