አርብ ጥቅምት 16/2016
የኔቶ አባል ሀገራት ደረጃውን የጠበቀ የጦር መሳሪያና ጥይት ምርታቸውን በከፍተኛ ደረጃ ይጨምሩ ዘንድ ጥሪ ቀርቦላቸዋል፡፡ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት /ኔቶ/ የወታደራዊ ኮሚቴ ሊቀመንበር አድሚራል ሮበርት ፒተር በሰጡት ማብራሪያ የድርጅቱ አባል ሀገራት የጦር መሳሪያና ጥይት ምርታቸውን በጥራትና በብዛት ያመርቱ ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ እንደ ሮበርት ሰፊ ማብራሪያ ዩክሬን ሩሲያን ከምድራቸው ለማስወጣት በየጊዜው የምትተኩሰው ጥይት መጠኑ እንዳይቀንስና ሩሲያም የበለጠ በዩክሬን ምድር ድል እንዳታስመዘግብ የኔቶ አባል ሀገራት የወታደራዊ ድጋፋቸውን አጠናክረው መቀጠል አለባቸው ነው ያሉት፡፡ ዘገባው፡-የኢውሮሜይዳን ነው፡፡
