ጥቅምት 16/ 2016
የአሜሪካ መከላከያ መሥሪያ ቤት ፔንታገን ባወጣው መግለጫ በአየር ድብደባው የተመቱት ወታደራዊ ተቋማት በኢራን እና የኢራን ተባባሪ በሆኑ ቡድኖች ጥቅም ላይ ሲውሉ የነበሩ ናቸው ብሏል።
በአገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር አርብ ንጋት ላይ በአሜሪካ ኤፍ-16 የጦር ጄቶች በተፈጸመው የአየር ጥቃት ኢራን ጦር መሳሪያ እና ተተኳሽ ለማከማችት የምትጠቀምበት ስፍራ ወድሟል ተብሏል።
የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን አአገራቸው ይህን እርምጃ የወሰደችው በኢራቅ እና ሶሪያ የሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሠራዊት አባላትን ለመጠበቅ እና በቅርቡ በኢራን የሚደገፉ ቡድኖች ላደረሱት ጥቃት ምላሽ ለመስጠት ነው ብለዋል።
መከላከያ ሚንስትሩ በኢራን የሚደገፉ ቡድኖች በአሜሪካ ጦር ሠራዊት ላይ የሚያደርሱት ጥቃት የማይቆም ከሆነ አሜሪካ አሁንም ተመሳሳይ እርምጃዎችን መውሰዷን ትቀጥላለች ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ዘገባው የቢቢሲ አማርኛ ነው፡፡
