አዲስ ጊዜ

227 Posts
ኢሰመኮ ሰሞኑን ያወጣሁትን መግለጫ ላይ ማስተካከያ አደርጋለሁ ብሏል፡፡

ኢሰመኮ ሰሞኑን ያወጣሁትን መግለጫ ላይ ማስተካከያ አደርጋለሁ ብሏል፡፡

አርብ ጥቅምት 15 /2016 ኢሰመኮ ሰሞኑን ባወጣው ኹለተኛው አገር ዓቀፍ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ሪፖርት ትግራይን አስመልክቶ የተሳሳተ መረጃ ማካተቱን ትናንት ምሽት ባወጣው እርማት አስታውቋል። ኮሚሽኑ በሪፖርቱ፣ በሰሜኑ ጦርነት የተፈናቀሉ በርካታ ሰዎች ወደቀያቸው እንደተመለሱና ጅምሩ መልካም ርምጃ እንደኾነ ገልጦ ነበር። ለሪፖርቱ የተሠራው ጥናት ትግራይን አያካትትም ነበር ያለው ኮሚሽኑ፣ የተሳሳተውን መረጃ ከክልሉ አስተዳደር ጋር በመተባበር እንደሚያጣራው ገልጧል።
ተጨማሪ ያንብቡ
በእስራኤል ድንበር የምትገኘው የግብጿ ከተማ በሚሳይል ተመታች።

በእስራኤል ድንበር የምትገኘው የግብጿ ከተማ በሚሳይል ተመታች።

አርብ ጥቅምት 16/2016 ሚሳይሉ በታባ የጤና ማዕከል ላይ ማረፉን እና ስድስት ሰዎችን ማቁሰሉ ተገልጿል እየተካሄደ ባለው የእስራኤል-ሀማስ ጦርነት ምክንያት የተተኮሰው ሚሳይል ከጋዛ ሰርጥ 220 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኘውን የግብጿን የመዝናኛ ከተማ መምታቱን ሮይተርስ ዘግቧል። ሚሳይሉ በታባ የጤና ማዕከል ላይ ማረፉን እና ስድስት ሰዎችን ማቁሰሉን ዘገባው ጠቅሷል። ታባ ግብጽን ከቀይ ባህሯ የእስራኤል ወደብ ኢላት የምታገናኝ ቦታ ነች። የእስራኤል ጦር ከድንበር ውጭ ስለተፈጠረው የጸጥታ ችግር መረጃ እንዳለው ገልጿል።ሀማስ በበኩሉ ባለፈው ሮብዕ እለት እንደገለጸው የእስራኤሏን ኢላት ኢላማ አድርጎ እንደነበር የገለጸ ቢሆንም የእስራኤል ጦር ከኢላት ወጣ ቦታ ማረፉን አስታውቋል።የእስራኤል-ሀማስ ግጭት ከተቀሰቀሰበት ባለፈው ጥቅምት ወዲህ ይህ የመጀመሪያው የረጅም ርቀት የፍልስጤም ጥቃት…
ተጨማሪ ያንብቡ
ሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት /ኔቶ/ አባል ሀገራቱ የጦር መሳሪያና ጥይት ያመርቱ ዘንድ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት /ኔቶ/ አባል ሀገራቱ የጦር መሳሪያና ጥይት ያመርቱ ዘንድ ጥሪ አቅርቧል፡፡

አርብ ጥቅምት 16/2016 የኔቶ አባል ሀገራት ደረጃውን የጠበቀ የጦር መሳሪያና ጥይት ምርታቸውን በከፍተኛ ደረጃ ይጨምሩ ዘንድ ጥሪ ቀርቦላቸዋል፡፡ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት /ኔቶ/ የወታደራዊ ኮሚቴ ሊቀመንበር አድሚራል ሮበርት ፒተር በሰጡት ማብራሪያ የድርጅቱ አባል ሀገራት የጦር መሳሪያና ጥይት ምርታቸውን በጥራትና በብዛት ያመርቱ ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ እንደ ሮበርት ሰፊ ማብራሪያ ዩክሬን ሩሲያን ከምድራቸው ለማስወጣት በየጊዜው የምትተኩሰው ጥይት መጠኑ እንዳይቀንስና ሩሲያም የበለጠ በዩክሬን ምድር ድል እንዳታስመዘግብ የኔቶ አባል ሀገራት የወታደራዊ ድጋፋቸውን አጠናክረው መቀጠል አለባቸው ነው ያሉት፡፡ ዘገባው፡-የኢውሮሜይዳን ነው፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
አሜሪካ በምሥራቃዊ ሶሪያ ውስጥ በሚገኙ ሁለት ወታደራዊ ተቋማት ላይ የአየር ደብድባ መፈጸሟን አስታወቀች።

አሜሪካ በምሥራቃዊ ሶሪያ ውስጥ በሚገኙ ሁለት ወታደራዊ ተቋማት ላይ የአየር ደብድባ መፈጸሟን አስታወቀች።

ጥቅምት 16/ 2016 የአሜሪካ መከላከያ መሥሪያ ቤት ፔንታገን ባወጣው መግለጫ በአየር ድብደባው የተመቱት ወታደራዊ ተቋማት በኢራን እና የኢራን ተባባሪ በሆኑ ቡድኖች ጥቅም ላይ ሲውሉ የነበሩ ናቸው ብሏል። በአገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር አርብ ንጋት ላይ በአሜሪካ ኤፍ-16 የጦር ጄቶች በተፈጸመው የአየር ጥቃት ኢራን ጦር መሳሪያ እና ተተኳሽ ለማከማችት የምትጠቀምበት ስፍራ ወድሟል ተብሏል። የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን አአገራቸው ይህን እርምጃ የወሰደችው በኢራቅ እና ሶሪያ የሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሠራዊት አባላትን ለመጠበቅ እና በቅርቡ በኢራን የሚደገፉ ቡድኖች ላደረሱት ጥቃት ምላሽ ለመስጠት ነው ብለዋል። መከላከያ ሚንስትሩ በኢራን የሚደገፉ ቡድኖች በአሜሪካ ጦር ሠራዊት ላይ የሚያደርሱት ጥቃት የማይቆም ከሆነ አሜሪካ አሁንም ተመሳሳይ እርምጃዎችን…
ተጨማሪ ያንብቡ
ከታገቱት 6 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ሰራተኞች መሃከል ሶስቱ ተለቀቁ::

ከታገቱት 6 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ሰራተኞች መሃከል ሶስቱ ተለቀቁ::

አርብ ጥቅምት 15 ቀን 2016 የኢትዮጽያ ኤሌክትሪክ ኃይል ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች ካገቷቸው ስድስት የአሉቶ የእንፋሎት ኃይል ፕሮጀክት ሠራተኞች መካከል ሦስቱ መለቀቃቸውን መናገሩን ዴይቸቨለ ዘግቧል። ከተለቀቁት ሠራተኞች ውስጥ አንዱ ኬንያዊ ነው ተብሏል።ቀሪዎቹን ታጋቾች የማስለቀቅ ጥረቱ መቀጠሉን ተቋሙ እንደገለጠ የጠቀሰው ዘገባው፣ ታጋቾቹ በምን አኳኋን እንደተለቀቁ ግን ተቋሙ አልገለጠም ብሏል። በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን የሚገኘው ፕሮጀክት ሠራተኞች በተሽከርካሪ ሲጓዙ የታገቱት ከሦስት ሳምንት በፊት ነበር።
ተጨማሪ ያንብቡ

በኢትዮጵያ ዓለማቀፉ የሰብዓዊ መብቶች መርማሪ ኮሚሽን በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ወንጀል የፈጸሙ አካላት በአለም አቀፍ ፍ/ቤቶች ተጠያቂ እንዲሆኑ ጠየቀ፡፡

አርብ ጥቅምት 15 /2016 በኢትዮጵያ ዓለማቀፉ የሰብዓዊ መብቶች መርማሪ ኮሚሽን አገራትና ተቋማት በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ወንጀሎችን የፈጸሙ አካላት በዓለማቀፍ ፍርድ ቤቶች ጭምር ተጠያቂ እንዲኾኑ ጥረት እንዲያደርጉ ረቡዕ'ለት ለተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ባቀረበው ሪፖርት ጠይቋል። ዓለማቀፉ ኅብረተሰብ የኢትዮጵያን የሰብዓዊ መብት ኹኔታ መከታተሉንና ለጦርነቱ ተጎጂዎች ድጋፍ መስጠቱን እንዳያቋርጥም ኮሚሽኑ አሳስቧል። ኮሚሽኑ፣ በአገሪቱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በቀጠሉበት ወቅት ቆይታ ጊዜው እንዲያበቃ መደረጉ ስህተት መኾኑንም ለተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ገልጧል።
ተጨማሪ ያንብቡ
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የኢሰመኮን ሪፖርት እንደማይቀበል ተናገረ፡፡

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የኢሰመኮን ሪፖርት እንደማይቀበል ተናገረ፡፡

አርብ ጥቅምት 15 /2016 የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የትግራይ ተፈናቃዮችን አስመልክቶ "ሐሰተኛ" ሪፖርት አውጥቷል በማለት ትናንት ማምሻውን ባወጣው ምላሽ ከሷል። የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች ከቤት ንብረታቸው በተፈናቀሉበት ወቅት ኮሚሽኑ ይህን ሪፖርት ማውጣቱ፣ "ኃላፊነት የጎደለው" እና "ዓለማቀፉን ኅብረተሰብ ለማሳሳት ኾን ተብሎ የተሠራ" ነው በማለት ወቅሷል።የክልሉ አስተዳደር አያይዞም፣ ፌደራል መንግሥቱ ወደፊት ተመሳሳይ ሪፖርቶች እንዳይወጡ፣ አስፈላጊውን ርምጃ እንዲወስድ ጠይቋል።
ተጨማሪ ያንብቡ
ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ‹‹ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥም ቢሆን በጋዜጠኞችና በመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ላይ የሚኖር ተጠያቂነት ህጋዊ ስርአትን የተከተለ ሊሆን ይገባል›› የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት

ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ‹‹ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥም ቢሆን በጋዜጠኞችና በመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ላይ የሚኖር ተጠያቂነት ህጋዊ ስርአትን የተከተለ ሊሆን ይገባል›› የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት

ጥቅምት 12 ፤2016 ፤አዲስ አበባ )  የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት በሥነ ምግባር የታነጸ በሃላፊነት ስሜት ህዝብን የሚያገለግል ሚዲያ በሀገራችን እንዲጎለብት የሚሰራ ተቋም ሲሆን፤ በሕግ ተመዝግበው ፈቃድ የወሰዱ የህዝብ ፤የንግድ፤ የማህበረሰብ መገናኛ ብዙሃንን፤የበይነ መረብ ሚዲያንና የጋዜጠኞች ሙያ ማህበራትን በአባልነት በማቀፍ የእርስ በእርስ የቁጥጥር ስርዓትን ተግባራዊ እያደረገ የሚገኝ ተቋም ነው፤ምክር ቤታችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማትና ጋዜጠኞች ላይ ከህግ አግባብ ውጪ አስሮ የማቆየትና ለስርጭት የተዘጋጀ የህትመት ውጤትን የማገድ ድርጊቶች እንደተፈፀመባቸውና በዚህም ሳቢያ ተቋማቱ የእለት ተዕለት ስራዎቻቸውን ለመስራት መቸገራቸውን ከደረሱት ሪፖርቶች ተገንዝቧል፡፡በኢትዮጵያ ሕገ መንግስት አንቀፅ 29 ንዑስ አንቀፅ 4 ላይ በግልፅ እንደተመለከተው ‹ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች፤ሃሳቦች፤አመለካከቶች በነፃ መንሸራሸራቸውን ለማረጋገጥ…
ተጨማሪ ያንብቡ