አዲስ ጊዜ

230 Posts
ምክር ቤቱ የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬን ጨምሮ የሦስት የምክር ቤት አባላትን ያለመከሰስ መብት አነሳ።

ምክር ቤቱ የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬን ጨምሮ የሦስት የምክር ቤት አባላትን ያለመከሰስ መብት አነሳ።

ጥቅምት 19/2016 የሲዳማ ክልል መንግስት ም/ቤት ዛሬ ባካሄደው 6ኛ ዙር 3ኛ የሤራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤው፤ የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የነበሩት ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬን ጨምሮ 3 የምክር ቤት አባላትን ያለመከሰስ መብት አንስቷል። በዚህም መሠረት የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕ/ሮ ፀጋዬ ቱኬ፣ ከሳቸው ጋር የዝምድና እና የጥቅም ትስስር እንዳላቸው የሚጠረጠሩት ተሰማ ደንጉሼ፣ እንዲሁም የቀድሞው የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮምሽነር የነበሩት አበራ አሬራ በሙስና ወንጀል በመጠርጠራቸው ምክንያት ምክር ቤቱ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ ውሳኔ አሳልፏል። ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ከቀናት በፊት ወደ አገር ሲገቡ ቦሌ ኤርፖርት ላይ በጸጥታ ኃይሎች ተይዘው በሀዋሳ በሚገኝ የእስረኞች ማቆያ ውስጥ እንደሚገኙ የክልሉ ፖሊስ ማሳወቁ…
ተጨማሪ ያንብቡ
የአማራ ክልል ሁሉም ዞኖች በተለያየ ደረጃና ጊዜ የትጥቅ ግጭት ተካሂዶባቸዋል ተባለ።

የአማራ ክልል ሁሉም ዞኖች በተለያየ ደረጃና ጊዜ የትጥቅ ግጭት ተካሂዶባቸዋል ተባለ።

ሰኞ ጥቅምት 19/2016 የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የአማራ ክልልን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ዛሬ ባሰራጨው ዘለግ ያለ ዘገባ ከ ሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም አንስቶ ባሉት ጊዜያት በአማራ  ክልል ሁሉም ዞኖች በተለያየ ደረጃና ጊዜ የትጥቅ ግጭት ተካሂዶባቸዋል ሲል ገልጿል። በተጨማሪም እነዚህ አካባቢዎች ወይም ወረዳዎች በአንድ ወቅት በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች፣ በሌላ ወቅት በታጣቂው ቡድን (በተለምዶ ፋኖ በመባል የሚታወቀው) ቁጥጥር ሥር ውለዋል። የትጥቅ ግጭቱ በአንዳንድ አካባቢዎች በከባድ መሣሪያ እና አልፎ አልፎ በአየር/ድሮን ድብደባ ጭምር የታገዘ ነው ሲል ገልጿል። በግጭቱ ዐውድ የአየር/ድሮን መሣሪያን ጨምሮ በከባድ መሣሪያዎች ጥቃት የተነሳ በሲቪል ሰዎች ላይ ሞት እና የአካል ጉዳት የደረሰ ሲሆን፣ ሰዎች መኖሪያ አካባቢያቸውን ጥለው…
ተጨማሪ ያንብቡ
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጥቅምት 15 ቀን 2016 ዓ.ም. የኮሚሽኑን 2ኛ ዓመታዊ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መብቶችን ሁኔታ በተመለከተ ያወጣውን መግለጫ በተመለከተኢሰመኮመግለጫአውጥቷል፡፡

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጥቅምት 15 ቀን 2016 ዓ.ም. የኮሚሽኑን 2ኛ ዓመታዊ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መብቶችን ሁኔታ በተመለከተ ያወጣውን መግለጫ በተመለከተኢሰመኮመግለጫአውጥቷል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጋዜጣዊ መግለጫ ጥቅምት 16 ቀን 2016 ዓ.ም.  የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) ጥቅምት 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ይፋ ያደረገውን ሁለተኛውን የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መብቶች ሁኔታ ሪፖርት በሚመለከት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ጥቅምት 15 ቀን 2016 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ የኮሚሽኑ ሪፖርት በጦርነት ምክንያት ተፈናቅለው የነበሩ የትግራይ ክልል ተፈናቃዮች በብዛት ወደ መኖሪያ አካባቢያቸው እንደተመለሱ እና ሰብአዊ ድጋፍ እየቀረበላቸው እንደሆነተደርጎ የተገለጸው ስሕተት ስለሆነ ሊስተካከል ይገባል በሚል መግለጹን ተከትሎ፣ ኢሰመኮ ወዲያውኑ በሰጠው አጭር ማብራሪያ ሪፖርቱ ይህንን መሰል መረጃ እንደማያካትት፣ የሪፖርቱ አካባቢያዊ ወሰን የትግራይ ክልልን እንደማይጨምር በሪፖርቱ የተገለጸ መሆኑንና በተሳሳተ አረዳድ ስለተሰራጨው የተሳሳተ መረጃና ተያያዥ ጉዳዮች በተመለከተ ኮሚሽኑ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር እንደሚነጋገር ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።   በዚህም መሠረት ኮሚሽኑ ከትግራይ…
ተጨማሪ ያንብቡ
ኢሰመኮ ሰሞኑን ያወጣሁትን መግለጫ ላይ ማስተካከያ አደርጋለሁ ብሏል፡፡

ኢሰመኮ ሰሞኑን ያወጣሁትን መግለጫ ላይ ማስተካከያ አደርጋለሁ ብሏል፡፡

አርብ ጥቅምት 15 /2016 ኢሰመኮ ሰሞኑን ባወጣው ኹለተኛው አገር ዓቀፍ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ሪፖርት ትግራይን አስመልክቶ የተሳሳተ መረጃ ማካተቱን ትናንት ምሽት ባወጣው እርማት አስታውቋል። ኮሚሽኑ በሪፖርቱ፣ በሰሜኑ ጦርነት የተፈናቀሉ በርካታ ሰዎች ወደቀያቸው እንደተመለሱና ጅምሩ መልካም ርምጃ እንደኾነ ገልጦ ነበር። ለሪፖርቱ የተሠራው ጥናት ትግራይን አያካትትም ነበር ያለው ኮሚሽኑ፣ የተሳሳተውን መረጃ ከክልሉ አስተዳደር ጋር በመተባበር እንደሚያጣራው ገልጧል።
ተጨማሪ ያንብቡ
በእስራኤል ድንበር የምትገኘው የግብጿ ከተማ በሚሳይል ተመታች።

በእስራኤል ድንበር የምትገኘው የግብጿ ከተማ በሚሳይል ተመታች።

አርብ ጥቅምት 16/2016 ሚሳይሉ በታባ የጤና ማዕከል ላይ ማረፉን እና ስድስት ሰዎችን ማቁሰሉ ተገልጿል እየተካሄደ ባለው የእስራኤል-ሀማስ ጦርነት ምክንያት የተተኮሰው ሚሳይል ከጋዛ ሰርጥ 220 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኘውን የግብጿን የመዝናኛ ከተማ መምታቱን ሮይተርስ ዘግቧል። ሚሳይሉ በታባ የጤና ማዕከል ላይ ማረፉን እና ስድስት ሰዎችን ማቁሰሉን ዘገባው ጠቅሷል። ታባ ግብጽን ከቀይ ባህሯ የእስራኤል ወደብ ኢላት የምታገናኝ ቦታ ነች። የእስራኤል ጦር ከድንበር ውጭ ስለተፈጠረው የጸጥታ ችግር መረጃ እንዳለው ገልጿል።ሀማስ በበኩሉ ባለፈው ሮብዕ እለት እንደገለጸው የእስራኤሏን ኢላት ኢላማ አድርጎ እንደነበር የገለጸ ቢሆንም የእስራኤል ጦር ከኢላት ወጣ ቦታ ማረፉን አስታውቋል።የእስራኤል-ሀማስ ግጭት ከተቀሰቀሰበት ባለፈው ጥቅምት ወዲህ ይህ የመጀመሪያው የረጅም ርቀት የፍልስጤም ጥቃት…
ተጨማሪ ያንብቡ
ሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት /ኔቶ/ አባል ሀገራቱ የጦር መሳሪያና ጥይት ያመርቱ ዘንድ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት /ኔቶ/ አባል ሀገራቱ የጦር መሳሪያና ጥይት ያመርቱ ዘንድ ጥሪ አቅርቧል፡፡

አርብ ጥቅምት 16/2016 የኔቶ አባል ሀገራት ደረጃውን የጠበቀ የጦር መሳሪያና ጥይት ምርታቸውን በከፍተኛ ደረጃ ይጨምሩ ዘንድ ጥሪ ቀርቦላቸዋል፡፡ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት /ኔቶ/ የወታደራዊ ኮሚቴ ሊቀመንበር አድሚራል ሮበርት ፒተር በሰጡት ማብራሪያ የድርጅቱ አባል ሀገራት የጦር መሳሪያና ጥይት ምርታቸውን በጥራትና በብዛት ያመርቱ ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ እንደ ሮበርት ሰፊ ማብራሪያ ዩክሬን ሩሲያን ከምድራቸው ለማስወጣት በየጊዜው የምትተኩሰው ጥይት መጠኑ እንዳይቀንስና ሩሲያም የበለጠ በዩክሬን ምድር ድል እንዳታስመዘግብ የኔቶ አባል ሀገራት የወታደራዊ ድጋፋቸውን አጠናክረው መቀጠል አለባቸው ነው ያሉት፡፡ ዘገባው፡-የኢውሮሜይዳን ነው፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
አሜሪካ በምሥራቃዊ ሶሪያ ውስጥ በሚገኙ ሁለት ወታደራዊ ተቋማት ላይ የአየር ደብድባ መፈጸሟን አስታወቀች።

አሜሪካ በምሥራቃዊ ሶሪያ ውስጥ በሚገኙ ሁለት ወታደራዊ ተቋማት ላይ የአየር ደብድባ መፈጸሟን አስታወቀች።

ጥቅምት 16/ 2016 የአሜሪካ መከላከያ መሥሪያ ቤት ፔንታገን ባወጣው መግለጫ በአየር ድብደባው የተመቱት ወታደራዊ ተቋማት በኢራን እና የኢራን ተባባሪ በሆኑ ቡድኖች ጥቅም ላይ ሲውሉ የነበሩ ናቸው ብሏል። በአገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር አርብ ንጋት ላይ በአሜሪካ ኤፍ-16 የጦር ጄቶች በተፈጸመው የአየር ጥቃት ኢራን ጦር መሳሪያ እና ተተኳሽ ለማከማችት የምትጠቀምበት ስፍራ ወድሟል ተብሏል። የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን አአገራቸው ይህን እርምጃ የወሰደችው በኢራቅ እና ሶሪያ የሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሠራዊት አባላትን ለመጠበቅ እና በቅርቡ በኢራን የሚደገፉ ቡድኖች ላደረሱት ጥቃት ምላሽ ለመስጠት ነው ብለዋል። መከላከያ ሚንስትሩ በኢራን የሚደገፉ ቡድኖች በአሜሪካ ጦር ሠራዊት ላይ የሚያደርሱት ጥቃት የማይቆም ከሆነ አሜሪካ አሁንም ተመሳሳይ እርምጃዎችን…
ተጨማሪ ያንብቡ
ከታገቱት 6 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ሰራተኞች መሃከል ሶስቱ ተለቀቁ::

ከታገቱት 6 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ሰራተኞች መሃከል ሶስቱ ተለቀቁ::

አርብ ጥቅምት 15 ቀን 2016 የኢትዮጽያ ኤሌክትሪክ ኃይል ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች ካገቷቸው ስድስት የአሉቶ የእንፋሎት ኃይል ፕሮጀክት ሠራተኞች መካከል ሦስቱ መለቀቃቸውን መናገሩን ዴይቸቨለ ዘግቧል። ከተለቀቁት ሠራተኞች ውስጥ አንዱ ኬንያዊ ነው ተብሏል።ቀሪዎቹን ታጋቾች የማስለቀቅ ጥረቱ መቀጠሉን ተቋሙ እንደገለጠ የጠቀሰው ዘገባው፣ ታጋቾቹ በምን አኳኋን እንደተለቀቁ ግን ተቋሙ አልገለጠም ብሏል። በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን የሚገኘው ፕሮጀክት ሠራተኞች በተሽከርካሪ ሲጓዙ የታገቱት ከሦስት ሳምንት በፊት ነበር።
ተጨማሪ ያንብቡ