የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጥቅምት 15 ቀን 2016 ዓ.ም. የኮሚሽኑን 2ኛ ዓመታዊ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መብቶችን ሁኔታ በተመለከተ ያወጣውን መግለጫ በተመለከተኢሰመኮመግለጫአውጥቷል፡፡
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጋዜጣዊ መግለጫ ጥቅምት 16 ቀን 2016 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) ጥቅምት 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ይፋ ያደረገውን ሁለተኛውን የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መብቶች ሁኔታ ሪፖርት በሚመለከት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ጥቅምት 15 ቀን 2016 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ የኮሚሽኑ ሪፖርት በጦርነት ምክንያት ተፈናቅለው የነበሩ የትግራይ ክልል ተፈናቃዮች በብዛት ወደ መኖሪያ አካባቢያቸው እንደተመለሱ እና ሰብአዊ ድጋፍ እየቀረበላቸው እንደሆነተደርጎ የተገለጸው ስሕተት ስለሆነ ሊስተካከል ይገባል በሚል መግለጹን ተከትሎ፣ ኢሰመኮ ወዲያውኑ በሰጠው አጭር ማብራሪያ ሪፖርቱ ይህንን መሰል መረጃ እንደማያካትት፣ የሪፖርቱ አካባቢያዊ ወሰን የትግራይ ክልልን እንደማይጨምር በሪፖርቱ የተገለጸ መሆኑንና በተሳሳተ አረዳድ ስለተሰራጨው የተሳሳተ መረጃና ተያያዥ ጉዳዮች በተመለከተ ኮሚሽኑ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር እንደሚነጋገር ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። በዚህም መሠረት ኮሚሽኑ ከትግራይ…
