በአምስት የኢትዮጵያ ክልሎች የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ተባብሰው መቀጠላቸውን ኢሰመኮ በምርመራ ማረጋገጡን አስታወቀ
በ-እታገኘሁ መኮነን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብች ኮሚሽን በኢትዮጵያ በአማራ ፣በኦሮሚያ ፣በማእከላዊ ኢትዮጵያ ፣በደቡብ ኢትዮጵያ እና በጋምቤላ ክልል ከሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. እስከ መስከረም ወር 2017 ዓ.ም. የተፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ዙሪያ ሪፖርት አውጥቷል፡፡ኮሚሽኑ በሪፖርቱ በኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ ሥጋቶች እና አሳሳቢ ሁኔታዎች መኖራቸው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ይህ የሩብ ዓመት የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት ግን በተለይ በግጭት ዐውድ ውስጥ ባሉ አካባቢዎች ላይ ልዩ ትኩረት በማድረግ በዋነኝነት ከፍተኛ በሆኑ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችና አሳሳቢነታቸው በቀጠሉ ጉዳዮች ላይ አተኩሮ የተሰራና ለሰብአዊ መብቶች ሁኔታ መሻሻል ምክረ ሐሳቦችን የሚያቀርብ ነው ብሏል። ሪፖርቱ በዳሰሳቸው አካባቢዎች በነጻነት ተንቀሳቅሶ የተሟላ ክትትልና ምርመራ ለማካሄድ ምቹ ሁኔታ ባለመኖሩ፣ በተቻለ መጠን…
