የቅድመ መደበኛ ስርዓተ ትምህርት ላይ ማሻሻያ ለማድረግ የሚያስችል ጥናት ይፋ ሆነ
ችልድረን ብሊቭ ህጻናትን፣ ቤተሰቦችን እና ማህበረሰብን በአለም አቀፍ ደረጃ ለማብቃት የሚሰራ አለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው፡፡ድርጅቱ ድህነትን እና ኢፍትሃዊነትን በማሸነፍ ላይ ያተኮረ ተልእኮ በመያዝ፣ በትምህርት ቤት ውስጥ ህፃናት ፣ በራስ መተማመንን እና የራሳቸውን የወደፊት ህይወት ለመቅረጽ የሚያስፈልጉ ክህሎቶችን እንዲያዳብሩ ይሰራል፡፡ችልድረን ብሊቭ የቻይልድ ፈንድ አሊያንስ አባል ነው፡፡ ቻይልድ ፈንድ በ70 ሃገራት ወደ 36 ሚሊዮን የሚጠጉ ሕፃናትን እና ቤተሰቦቻቸውን በጋራ የሚደግፍ ዓለም አቀፍ ኔትወርክ ነው፡፡ ከ1987 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ስራ የጀመረው ድርጅቱ እንደ ቅድመ ልጅነት እንክብካቤ እና ልማት ፣ የእናቶች እና ህጻናት ጤና እና ስነ-ምግብ ፣ የወጣቶች ስራ ስምሪት ላይ እየሰራ ያለ ተቋም ነው፡፡ እ.ኤ.አ. በ…
