አዲስ ጊዜ

227 Posts
“የሚዲያ አዋጅ ማሻሻያ ” ወደፊት ወይስ ወደኋላ ?

“የሚዲያ አዋጅ ማሻሻያ ” ወደፊት ወይስ ወደኋላ ?

እታገኘሁ መኮነን የ2010ሩ ለውጥ እና የሚዲያው መነቃቃት 2010 ዓ.ም  ፤የጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድን ወደ ስልጣን መምጣት ተከትሎ በኢትዮጵያ የፖለቲካ እና የሃገር ግንባታ ሂደት ላይ ከታዩት ለውጦች  መሃል አንዱ ለሚዲያው አንጻራዊ የሚባል ነጻ የመጫወቻ ሜዳ መፍቀድ ነበር ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም  2013 ላይ የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ፀደቀ ፤የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013፡፡ ይሄ አዋጅ ከዛ ቀደም ብሎ ለ10 ዓመታት ያህል የሰራበትን የጋዜጠኝነት ሙያ በአፈና፣ በነጻነት ሃሳብን እና እውነትን መዘገብን በመነፈግ፣ በጫና እና ባለመመቸት ምክንያት ጥሎ ለመውጣት ለተገደደው ጋዜጠኛ ካህሳይ ብሩ እና የሙያ አጋሮቹ እንዲሁም ለመላው የሚዲያ ማህበረሰብ ፤ከዚያም ከፍ ሲል ደግሞ ሃሳብን በነፃነት በመግለፅ ለሚያምኑ ለዚህም ለሚተጉ የሰብዓዊ…
ተጨማሪ ያንብቡ
ምዕራብና የደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደሚኖራቸው ተተነበየ

ምዕራብና የደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደሚኖራቸው ተተነበየ

ይህ ይፋ የተደረገው የኢትዮጲያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት የወቅቱን ትንበያ ይፋ ለማድረግ ባዘጋጀው የባለድርሻ አካለት መድረክ ነው። በመድረኩም ያለፈውን የበጋ ወቅት ትንበያ የገመገመ ሲሆን በጋው በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ መደበኛ እና ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደተስተዋለባቸውና ይህም ሁኔታ በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው ለሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ ለሚገኙ አርሶ እና አርብቶ አደሮች ምቹ ሁኔታን የፈጠረ እንደነበረ ተገልጿል፡፡ በእለቱ የመጪው በልግ ትንበያ ይፋ የተደረገ ሲሆን በልግ ዋነኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሶማሌ ክልል ደቡባዊ ክፍል መደበኛና ከመደበኛ በታች፤ የቦረናና ጉጂ ዞኖች፤ የሲዳማ፤ የማዕከላዊና የደቡብ ኢትዮጵያ መደበኛና ከመደበኛ በላይ፤ በሌላ በኩል የደቡብ ትግራይ፤ የምስራቅ አማራ፤ አፋር፤ መካከለኛው እና የምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ መደበኛና…
ተጨማሪ ያንብቡ
ከተመን በላይ ነዳጅ የሚሸጡ ነጋዴዎችን እስከ አምስት አመት እስር እና እስከ 500 ሺህ ብር የሚያስቀጣ አዋጅ ጸደቀ፡፡አዋጁ ከምክር ቤት አባላት ጠንካራ ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡

ከተመን በላይ ነዳጅ የሚሸጡ ነጋዴዎችን እስከ አምስት አመት እስር እና እስከ 500 ሺህ ብር የሚያስቀጣ አዋጅ ጸደቀ፡፡አዋጁ ከምክር ቤት አባላት ጠንካራ ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ጥር 1 ቀን 2017 ባካሄደው ስብሰባ  መንግሥት ከተመነው የመሸጫ ዋጋ በላይ ሲሸጡ የተገኙ ነጋዴዎች  ከሦስት ዓመት እስከ አምስት ዓመት የሚደርስ የእስር ቅጣት እና እስከ አምስት መቶ ሺህ ብር እንዲቀጡ የሚያደርግ አዋጅ  አጽድቋል፡፡ በአዋጁ መሠረት ከመሸጫ ዋጋ በላይ በመሸጥ የሚፈጸም የመጀመሪያ ጥፋት ከሦስት መቶ ሃምሳ ሺህ እስከ አምስት መቶ ሺህ ብር ያስቀጣል።ድርጊቱ በተደጋጋሚ ከተፈጸመ ከገንዘብ ቅጣት በተጨማሪ ከሦስት ዓመት እስከ አምስት ዓመት የሚደርስ የእስር ቅጣት እንደሚኖር በአዋጁ ተደንግጓል። ድርጊቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲፈጸም  ከ300 ሺህ እስከ 500 ሺህ ብር የሚያስቀጣ ሲሆን፣ በተደጋጋሚ ከተፈጸመ ከሦስት ዓመት እስከ አምስት ዓመት እስራት እና ከ350 ሺህ እስከ…
ተጨማሪ ያንብቡ
በአተገባበሩ ላይ ተቃውሞ ይቀርብበት የነበረውን የሚዲያ አዋጅ ለማሻሻል የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተቃውሞ ቀረበ፡፡

በአተገባበሩ ላይ ተቃውሞ ይቀርብበት የነበረውን የሚዲያ አዋጅ ለማሻሻል የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተቃውሞ ቀረበ፡፡

ረቂቅ አዋጁን በመቃወም 14 የጋዜጠኝነት ሙያ ማህበራት እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች የጋራ መግለጫ አውጥተዋል፡፡ እታገኘሁ መኮነን ከሁለት ሳምንት በፊት ጥቅምት 19ቀን2017 ዓ.ም የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ6ኛው ዙር 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ባካሄደው 2ኛ መደበኛ ስብሰባ፣የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013ን ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ለዝርዝር እይታ ለዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መምራቱ የሚታወቅ ነው፡፡ በዚህ ረቂቅ አዋጅ ላይ 14  የጋዜጠኝነት የሙያ ማህበራት እና የሰብዓዊ መብት ድርጅቾች የአዋጁ ማሻሻያ አስፈላጊነት ላይ ገለልተኛ ጥናት ባልተደረገበት፣ በቂ የባለድርሻ አካላት ውይይትም ባልተካሔደበት ሁኔታ ረቂቁ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲፀድቅ መቅረቡ፣ እንዲሁም በአዋጁ ከለላ ተሰጥቷቸው የነበሩ የቁጥጥርና…
ተጨማሪ ያንብቡ
በአምስት የኢትዮጵያ ክልሎች የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ተባብሰው መቀጠላቸውን ኢሰመኮ በምርመራ ማረጋገጡን አስታወቀ

በአምስት የኢትዮጵያ ክልሎች የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ተባብሰው መቀጠላቸውን ኢሰመኮ በምርመራ ማረጋገጡን አስታወቀ

      በ-እታገኘሁ መኮነን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብች ኮሚሽን በኢትዮጵያ በአማራ ፣በኦሮሚያ ፣በማእከላዊ ኢትዮጵያ ፣በደቡብ ኢትዮጵያ እና በጋምቤላ ክልል ከሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. እስከ መስከረም ወር 2017 ዓ.ም. የተፈፀሙ  የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ዙሪያ ሪፖርት አውጥቷል፡፡ኮሚሽኑ በሪፖርቱ  በኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ ሥጋቶች እና አሳሳቢ ሁኔታዎች መኖራቸው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ይህ የሩብ ዓመት የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት ግን በተለይ በግጭት ዐውድ ውስጥ ባሉ አካባቢዎች ላይ ልዩ ትኩረት በማድረግ በዋነኝነት ከፍተኛ በሆኑ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችና አሳሳቢነታቸው በቀጠሉ ጉዳዮች ላይ አተኩሮ የተሰራና  ለሰብአዊ መብቶች ሁኔታ መሻሻል ምክረ ሐሳቦችን የሚያቀርብ ነው ብሏል።  ሪፖርቱ በዳሰሳቸው አካባቢዎች በነጻነት ተንቀሳቅሶ የተሟላ ክትትልና ምርመራ ለማካሄድ ምቹ ሁኔታ ባለመኖሩ፣ በተቻለ መጠን…
ተጨማሪ ያንብቡ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከነገ ነሃሴ 28 ጀምሮ ወደ ኤርትራ መብረር ያቆማል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከነገ ነሃሴ 28 ጀምሮ ወደ ኤርትራ መብረር ያቆማል፡፡

አየር መንገዱ ከአዲስ አበባ አስመራ እና ከአስመራ ወደ አዲስ አበባ ሲያደርግ የነበረውን በረራ ማቋረጡን ፋ ያደረገ ሲሆን አስቀድመው የበረራ ጉዞ ቲኬት የቆረጡ መንገደኞች  ግን ያለምንም ዋጋ ጭማሪ በሌሎች አየር መንገዶች እንዲጓዙ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባወጣው መግለጫ ከነገ ነሀሴ 28 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንደሚያቆም አስታውቋል፡፡ ከአዲስ አበባ ወደ አስመራ እና ከአስመራ ወደ አዲስ አበባ የሚደረጉ በረራዎችን አቋርጫለሁ ያለው አየር መንገዱ በኤርትራ ያለው አሰራር አስቸጋሪ እና ከቁጥጥሩ ውጪ መሆኑ ለበረራው መቋረጥ በምክንያትነት ተጠቅሷል፡፡ ጉዞ ለማድረግ ቲኬት የገዙ መንገደኞችም በመረጡት አየር መንገዶች እንዲበሩ እንደሚያደርግ እና የዋጋ ጭማሪ እንደማያደርግም አየር መንገዱ ገልጿል፡፡ ኤርትራ…
ተጨማሪ ያንብቡ
ሌሎች አካላት ቀጠናውን ለማተራመስ ሲንቀሳቀሱ ኢትዮጵያ ቆማ እንደማትመለከት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ

ሌሎች አካላት ቀጠናውን ለማተራመስ ሲንቀሳቀሱ ኢትዮጵያ ቆማ እንደማትመለከት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ማምሻውን ባወጣው ባወጣው መግለጫው ሌሎች አካላት ቀጠናውን ለማተራመስ ሲንቀሳቀሱ ኢትዮጵያ ቆማ እንደማትመለከት አስታውቋል። መግለጫው የወጣው በትናንትናው እለት የግብፅ የጦር አውሮፕላኖች ወደ ሶማልያ መዲና ሞቃዲሾ ቀሳቁስ እና ወታደሮችን ማጓጓዛቸው ይፋ ከሆነ በኋላ ነው። "ኢትዮጵያ ብሄራዊ ፀጥታዋን ሊያውኩ የሚችሉ በቀጠናው እየተከናወኑ ያሉ ድርጊቶችን በንቃት እየተከታተለች ነው" ያለው መግለጫው የሶማልያ መንግስት ከውጫዊ ሀይሎች ጋር በማበር ቀጠናው ላይ ውጥረት እየፈጠረ ነው ብሎ ከሷል። መግለጫው አክሎም "ለአጭር ግዜ እና እርባና ቢስ ጥቅም ብለው አካባቢው ላይ ውጥረት የሚነዙ ሀይሎች ለድርጊታቸው ተጠያቂ ይሆናሉ" ብሏል። ይሁንና መግለጫው በትናንትናው እለት አውሮፕላኖችን ወደ ሶማልያ ያሰማራችውን ግብፅን በስም አልጠቀሰም። የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና…
ተጨማሪ ያንብቡ
በሚቀጥሉት 20 ቀናት በሚኖረው ከባድ ዝናብ የመሬት መንሸራተት አደጋ ሊያጋጥም ይችላል – ሚቲዎሮሎጂ

በሚቀጥሉት 20 ቀናት በሚኖረው ከባድ ዝናብ የመሬት መንሸራተት አደጋ ሊያጋጥም ይችላል – ሚቲዎሮሎጂ

በሚቀጥሉት 20 ቀናት በሚጥለው ከባድ ዝናብ የተነሳ ቅጽበታዊ ጎርፍ፣ የመሬት መንሸራተት እና የወንዞች ሙላት ሊያጋጥም ይችላል ሲል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስጠነቀቀ። በሚቀጥሉት 10 ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት በዓባይ፣ ተከዜ፣ ባሮአኮቦ፣ ኦሞ፣ ጊቤ፣ አዋሽ፣ አፋር ደናክል፣ የላይኛውና የመካከለኛው ስምጥ ሸለቆ፣ የላይኛው የገናሌ ዳዋና ዋቤ ሸበሌ ተፋሰሶች መካከለኛና በጣም ከፍተኛ እርጥበት እንደሚኖራቸው ጠቁሟል። ተዳፋታማ በሆኑ አካባቢዎች የመሬት መንሸራተትና መሰንጠቅ፣ እንዲሁም የሰብል በጎርፍ የመጠረግ ሁኔታዎች እንዳይኖር መጠንቀቅ ያስፈልጋል ሲል ኢንስቲትዩቱ አሳስቧል። እርጥበት በሚበዛባቸው አካባቢዎችም የሰብል በሽታ እንዳይከሰት ቅድመ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባም ጠቁሟል። በተጨማሪም በሚቀጥሉት 8 ቀናት በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን፣ በሰሜን ምስራቅ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች አልፎ አልፎ…
ተጨማሪ ያንብቡ
ጋዜጠኞች ለሚያጋጥማቸው የመብት ጥሰት ጥብቅና የሚቆም እና የህግ ድጋፍ አገልግሎት የሚሰጥ የጋዜጠኞች  እና የሕግ ባለሙያዎች ጥምረት ሊመሰረት ነው፡፡

ጋዜጠኞች ለሚያጋጥማቸው የመብት ጥሰት ጥብቅና የሚቆም እና የህግ ድጋፍ አገልግሎት የሚሰጥ የጋዜጠኞች  እና የሕግ ባለሙያዎች ጥምረት ሊመሰረት ነው፡፡

እታገኘሁ መኮነን MELA ( Media Lawyers alliance )ተብሎ የተሰየመው ይህ የሚዲያ እና የህግ ባለሞያዎች ጥምረት በምስረታ ሂደት ላይ መሆኑን ከኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ኅብረት (ኢሰመድኅ) ሰምተናል፡፡ ኅብረቱ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) ጋር በመሆን  በጥምረቱ ዙሪያ  ትናንት ማክሰኞ ነሀሴ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ውይይት አዘጋጅቶ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ኅብረት (ኢሰመድኅ)  ዳሬክተር አቶ መስዑድ ገበየሁ ጥምረቱ  የጋዜጠኝነት ሙያ ማህበራትን ማገዝ፣ጋዜጠኞች በሰሩት ስራ ለሚያጋጥማቸው የመብት ጥሰት እና ጫና የሕግ ድጋፍ የመሰጠት፣ለጋዜጠኞች መታሰር ምክንያት የሆኑ ጉዳዮች ላይ ጥናትና ምርምር የማድረግ፣ በመገናኛ ብዙኃን ዙሪያ  ህጎች ሲወጡ በባለሞያዎች ጥናት ማስጠናት እና ግብዓት ማቅረብ እንዲሁም በሚዲያው ህብረተሰብ…
ተጨማሪ ያንብቡ
 በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች አስቸኳይ ፍትህ እንዲያገኙ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ማህበር ጠይቋል።

 በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች አስቸኳይ ፍትህ እንዲያገኙ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ማህበር ጠይቋል።

ማህበሩ የጋዜጠኞቹ የፍርድ ሂደትም ከፖለቲካ አተያይ በፀዳ መንገድ እንዲሆን ጥሪ አቅርቧል። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር አዲስ ሥራ አስፈጻሚ አባላት በአዲስ አበባ ቃሊቲና ቂሊንጦ ማረሚያ ቤቶች በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞችን መጎብኘታቸውን ትናንት ባወጡት መግለጫ አሳውቀዋል፡፡ በጉብኝታቸውም ስለ ማረሚያ ቤት አያያዝ እና አጠቃላይ የፍትህ ሂደቱ ያለበትን ሁኔታ ከጋዜጠኞቹ ጋር እንደተወያዩ ማህበሩ በመግለጫው ላይ ጠቅሷል፡፡ በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞች በፖሊስ ቁጥጥር ስር በተያዙበት ወቅት የተያዙበት መንገድም ሆነ ከተያዙ በኃላ ያለው የፍርድ ቤት ሂደት አግባብነት እንደሚጎድለው ተናግረዋል፡፡ በሁለቱም ማረሚያ ቤቶች ከሁለት ዓመት በላይ ሳይፈረድባቸው የታሰሩ ጋዜጠኞች መኖራቸውን ማኅበሩ እንዳረጋገጠ አስታውቋል። ስለሆነም በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች እንዲፈቱ እንዲሁም የሚዲያ ምህዳሩ…
ተጨማሪ ያንብቡ