“የሚዲያ አዋጅ ማሻሻያ ” ወደፊት ወይስ ወደኋላ ?
እታገኘሁ መኮነን የ2010ሩ ለውጥ እና የሚዲያው መነቃቃት 2010 ዓ.ም ፤የጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድን ወደ ስልጣን መምጣት ተከትሎ በኢትዮጵያ የፖለቲካ እና የሃገር ግንባታ ሂደት ላይ ከታዩት ለውጦች መሃል አንዱ ለሚዲያው አንጻራዊ የሚባል ነጻ የመጫወቻ ሜዳ መፍቀድ ነበር ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም 2013 ላይ የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ፀደቀ ፤የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013፡፡ ይሄ አዋጅ ከዛ ቀደም ብሎ ለ10 ዓመታት ያህል የሰራበትን የጋዜጠኝነት ሙያ በአፈና፣ በነጻነት ሃሳብን እና እውነትን መዘገብን በመነፈግ፣ በጫና እና ባለመመቸት ምክንያት ጥሎ ለመውጣት ለተገደደው ጋዜጠኛ ካህሳይ ብሩ እና የሙያ አጋሮቹ እንዲሁም ለመላው የሚዲያ ማህበረሰብ ፤ከዚያም ከፍ ሲል ደግሞ ሃሳብን በነፃነት በመግለፅ ለሚያምኑ ለዚህም ለሚተጉ የሰብዓዊ…
