ቀይባህር

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ወደ ሳዑዲ አረቢያ አቀኑ

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ወደ ሳዑዲ አረቢያ አቀኑ

ኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሳዑዲ አረቢያ የአፍሪካ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ወደሪያድ አቅንተዋል። የአገሪቱ የመረጃ ሚኒስትር የማነ ገብረ መስቀል በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው እንዳሰፈሩት ኢሳያስ ዛሬ ማለዳ ላይ ወደ ሳዑዲ አምርተዋል። አብረዋቸው ከተጓዙ የልዑካን ቡድናቸው አባላት መካከል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው ኦስማን ሳለህ፥ የፓርቲያቸው የምጣኔ ኃብት ጉዳዮች ኃላፊ ሃጎስ ገብረህይወት እንዲሁም የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ ነስረዲን ቤኪት ይገኙበታል። በጉባዔው ይታደማሉ ተብሎ ከሚጠበቁ ሌሎች የአፍሪካ መሪዎች መካከልም የኬንያው ዊሊያም ሩቶ እና የናይጄሪያው ቦላ ቲኑቡ ይገኙበታል። የሳዑዲ አረቢያ የአፍሪካ ጉባዔ ሪያድ ከተለያዩ የአህጉሪቷ አገራት እንዲሁም የአፍሪካ ኅብረትን ከመሳሰሉ ተቋማት ጋር ያላትን ግንኙነት የምታጠናክርበት ነው። ጉባኤው ተፋፍሞ የቀጠለው የጋዛ ቀውስ ጥላ ያጠላበታል ተብሎ…
ተጨማሪ ያንብቡ
ኬንያ የሁሉም የአፍሪካ አገራት ዜጎች ያለቪዛ ወደ አገሯ እንዲገቡ ልትፈቅድ ነው።

ኬንያ የሁሉም የአፍሪካ አገራት ዜጎች ያለቪዛ ወደ አገሯ እንዲገቡ ልትፈቅድ ነው።

ኬንያ የቪዛ ገደቦችን በማንሳት ሁሉም አፍሪካውያን ቪዛ ሳያስፈልጋቸው ወደ ግዛቷ መግባት እንዲችሉ በሯን ለመክፈት መዘጋጀቷን ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ገለጹ። “አሁን የቪዛ ክልከላዎች አሉታዊ ተጽዕኖ እየፈጠሩብን መሆኑን የተገነዘብንበት ወቅት ነው” ሲሉ ፕሬዝዳንቱ በዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ላይ መናገራቸውን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል። ይህ ለአፍሪካውያን የቪዛ ጥያቄን ለማስቀረት የሚያስችለው የኬንያ ሃሳብ ባለንበት የአውሮፓውያን ዓመት ማብቂያ፣ ማለትም በመጪዎቹ ሁለት ወራት ተግባራዊ እንደሚሆን ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ገልጸዋል። በአህጉሪቱ አገራት መካከል ከቪዛ ነጻ ጉዞ እንዲኖር ማድረግ ከአፍሪካ ኅብረት ያለፉት ዓመታት ግቦች አንዱ ነበር።በ2022 (እአአ) በወጣ አንድ ሪፖርት መሠረት ሲሸልስ፣ ጋምቢያ እና ቤኒን ብቻ ናቸው እስካሁን ለአህጉሪቱ ዜጎች ከቪዛ ነጻ ጉዞን የፈቀዱት። ፕሬዝዳንት ሩቶ…
ተጨማሪ ያንብቡ
የሱዳንን ቀውስ ለመፍታት በአዲስ አበባ ጉባዔ ተዘጋጀ

የሱዳንን ቀውስ ለመፍታት በአዲስ አበባ ጉባዔ ተዘጋጀ

ቅዳሜ ጥቅምት 10/2016 በጎረቤት ሱዳን የተፈጠረውን ቀውስ ለመፍታት ያለመ እና የሱዳን ሲቪል ተቋማት የሚሳተፉበት ጉባዔ ከዛሬ ጥቅምት 10 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለአራት ቀናት በአዲስ አበባ እንደሚያካሄድ ተገለጸ። የሱዳን ሲቪል ሀይሎች በአዲስ አበባ በሚያካሂዱት በዚህ ጉባዔ ዋነኛ ትኩረት የሚሆነው በሀገሪቱ ለስድስት ወራት የዘለቀውን ግጭት እልባት ለመስጠት የሚያስችል ስልት መቀየስ መሆኑን ታማዙጂ ራዲዮ በድረገጹ ላይ በሰራው ዘገባ ጠቁሟል። በሳምንቱ መጨረሻ በአዲስ አበባ የሚደረገውን ጉባዔ ለማሳለጥ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑን ከተሳታፊዎች አንዱ የሆነው ኡማ ፓርቲ የሚዲያ ሃላፊ ሚስባህ አህመድ መሃመድ አረጋግጠዋል። ጉባዔው ከ70 በላይ የሚሆኑ የተለያዩ የሱዳን ሲቪል ተቋማትን እና ማህበረሰብ አንቂዎችን ተሳታፊ እንደሚያደርግ ተጠቁሟል።   የጉባዔው ዋነኛ ግብ በቀጣይ ወር…
ተጨማሪ ያንብቡ
የሶማሊያው አውዳል ራስ ገዝ ግዛት የኢትዮጵያን የወደብ ጥያቄ እንደሚቀበል ገለፀ

የሶማሊያው አውዳል ራስ ገዝ ግዛት የኢትዮጵያን የወደብ ጥያቄ እንደሚቀበል ገለፀ

ጥቅምት 07/2016 (ቀይ ባሕር) ከሱማሊላንድ በመነጠል ከሀገረ ሶማሊያ ጋር አንድነት ለመፍጠር እየታገለ ያለው የአውዳል ግዛት ንቅናቄ፣ ኢትዮጵያ በዘይላ ወደብ በኩል ወደ ቀይ ባህር ለመቅረብ ፍላጎት ካላት ሙሉ ትብብር እንደሚያደርግ ገለጸ፡፡ ንቅናቅው ትናንት ባወጣው ዝርዝር መግለጫ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ከሰሞኑ የሰጡትን ማብራርያ እንዳጤነው ዘርዝሮ “ይህን ህልማቸውን ለማሳካት  በይፋ ግብዣ አቀርባለው” ሲል የጠቅላይ ሚንስትሩ ሀሳብ ተጋሪ መሆኑን አረጋግጧል፡፡ የአውዳል ግዛት ንቅናቄ፣ ታሪካዊው የዘይላ ወደብ ለኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ክፍት እንደሚሆን እና ይህም በመግባቢያ ሰነድ እንደሚፀና በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አብራርŸል፡፡ ጨምሮም ይህ  ሂደት ሁሉንም ወገን አሸናፊ ያደርጋል ሲል ደምድሟል፡፡ ይህ የአውዳል ግዛት ንቅናቄ መግለጫ በሶማሊያውያን ዘንድ መነጋገርያ እየሆነ…
ተጨማሪ ያንብቡ
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ልዩ መልእክተኛ ኢትዮጵያን አስጠነቀቁ

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ልዩ መልእክተኛ ኢትዮጵያን አስጠነቀቁ

በሰብአዊ እርዳታ ጉዳይ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ልዩ መልእክተኛ የሆኑት እና በፓርላማ አባልነታቸው የሚታወቁት አብድል ራህማን አብድል ሻኩር ዋርሳሚ ኢትዮጵያ በሶማሊያ ባህር ላይ ላሳየቸው ፍላጎት ምላሽ የሚሆን ማስጠንቀቂያ አሰምተዋል፡፡ ዋርሳሚ በሃይልም ሆነ በማታለል ወደብ ለማግኘት የሚደረገው ሙከራ ተቀባይነት የለውም ሲሉ መናገራቸውን የሶማሊያ ዜና ምንጮች በስፋት ዘግበዋል፡፡ በሶማልያ ህዝብ እና አመራር ስም በወጣው በዚህ የዋርሳሚ መግለጫ ጉዳዩን በንቃት መከታተል እንደሚገባ አብራርቶ የሀገሪቱ መንግስት ጉዳዩን በቅርበት እንዲከታተል ያሳስባል፡፡ የፕሬዝዳንቱ ልዩ መልእክተኛ በማሳሰቢያቸው የባህር በር ህጋዊ ባለቤትነትን በሚመለከት ከኢትዮጵያ መንግስት አመራሮች እየተሰሙ ያሉት ተከታታይ መልእክቶች በቸልታ የሚታለፉ አይደሉም ሲሉ አበክረው ገልጸዋል፡፡ ይህ የአማካሪው ማሳሰቢያ የተሰማው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሶማሊያዋ ዘይላ…
ተጨማሪ ያንብቡ
ኤርትራ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ በቀሰቀሱት የቀይ ባህር ጉዳይ ምላሽ ሰጠች

ኤርትራ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ በቀሰቀሱት የቀይ ባህር ጉዳይ ምላሽ ሰጠች

በ-መርሻ ጥሩነህ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ከሰሞኑ የቀይ ባህርን ጉዳይ በአደባባይ አጀንዳ ማድረጋቸውን ተከትሎ፣ ኤርትራ ለጉዳዩ ምላሽ መግለጫ አውጥታለች፡፡ ኤርትራ በኢንፎርሜሽን ሚኒስቴሯ በኩል ባወጣችው አጭር መግለጫ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በባህር በር ጉዳይ እያራመዱት ያለው አቋም ጉዳዩ የሚመለከታቸውን አካላት ሁሉ ግራ ያጋባ መሆኑን አስታውቃለች፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በባህር በርና ተዛማጅ ጉዳዮች ላይ የተነሳው አጀንዳ ሰፊና ከመጠን በላይ የተራገበ መሆኑንም ጠቁማለች፡፡ ሁኔታው ግራ እንዳጋባት የገለጸችው ኤርትራ፣ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ በጉዳዩ አጀንዳ መሆን አንዳይበሳጩ አሳስባለች፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ የተለያዩ አካላትን ስለ ጉዳዩ በማስረዳት ውስጥ ለውስጥ ሲያብላሉት ከርመው በይፋ አደባባይ ካወጡት በኋላ፣ ከኤርትራ በኩል ከፍተኛ ቁጣ ተሰምቷል፡፡ በጉዳዩ ላይ…
ተጨማሪ ያንብቡ