የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ልዩ መልእክተኛ ኢትዮጵያን አስጠነቀቁ
በሰብአዊ እርዳታ ጉዳይ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ልዩ መልእክተኛ የሆኑት እና በፓርላማ አባልነታቸው የሚታወቁት አብድል ራህማን አብድል ሻኩር ዋርሳሚ ኢትዮጵያ በሶማሊያ ባህር ላይ ላሳየቸው ፍላጎት ምላሽ የሚሆን ማስጠንቀቂያ አሰምተዋል፡፡ ዋርሳሚ በሃይልም ሆነ በማታለል ወደብ ለማግኘት የሚደረገው ሙከራ ተቀባይነት የለውም ሲሉ መናገራቸውን የሶማሊያ ዜና ምንጮች በስፋት ዘግበዋል፡፡ በሶማልያ ህዝብ እና አመራር ስም በወጣው በዚህ የዋርሳሚ መግለጫ ጉዳዩን በንቃት መከታተል እንደሚገባ አብራርቶ የሀገሪቱ መንግስት ጉዳዩን በቅርበት እንዲከታተል ያሳስባል፡፡ የፕሬዝዳንቱ ልዩ መልእክተኛ በማሳሰቢያቸው የባህር በር ህጋዊ ባለቤትነትን በሚመለከት ከኢትዮጵያ መንግስት አመራሮች እየተሰሙ ያሉት ተከታታይ መልእክቶች በቸልታ የሚታለፉ አይደሉም ሲሉ አበክረው ገልጸዋል፡፡ ይህ የአማካሪው ማሳሰቢያ የተሰማው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሶማሊያዋ ዘይላ…
